በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ቁርኣን 22፥34 ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

"ተዋዱዕ تَوَاضُع የሚለው ቃል "ተዋደዐ" تَوَاضَعَ ማለትም "ተናነሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መተናነስ"humility" ወይም "ትህትና"humbles" ማለት ነው፦

ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 135
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሶደቃህ ሀብትን አይቀንስም፣ አሏህ አንድን ሰው ይቅርታ በማለቱ ክብርን እንጂ ሌላን አይጨምርለትም፣ አሏህ ከፍ የሚደርገው ቢሆን እንጂ ለአሏህ ራሱን የሚተናነስ የለም"።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَا نَقَصَتْ صَدَقَةٌ مِنْ مَالٍ وَمَا زَادَ اللَّهُ رَجُلاً بِعَفْوٍ إِلاَّ عِزًّا وَمَا تَوَاضَعَ أَحَدٌ لِلَّهِ إِلاَّ رَفَعَهُ اللَّهُ ‏"‏ ‏.‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "የሚተናነስ" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ተዋደዐ" تَوَاضَعَ ሲሆን ተዋዱዕ የሌለው ልብ ላይ ነቢያችን"ﷺ" ኢሥቲዓዛ አርገዋል፦

ሡነን አን-ነሣኢ መጽሐፍ 50, ሐዲስ 15
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ከአራት ነገር በአሏህ ይጠበቁ ነበር፥ እነርሱም ከማይጠቅም ዕውቀት፣ ከማይተናነስ ልብ፣ ከማይሰማ ዱዓእ እና ከማትረካ ነፍስ ናቸው"።
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَتَعَوَّذُ مِنْ أَرْبَعٍ مِنْ عِلْمٍ لاَ يَنْفَعُ وَمِنْ قَلْبٍ لاَ يَخْشَعُ وَدُعَاءٍ لاَ يُسْمَعُ وَنَفْسٍ لاَ تَشْبَعُ ‏.‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "ማይተናነስ" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ላ የኽሸዑ" لاَ يَخْشَعُ ሲሆን የስም መደቡ "ኹሹዕ" خُشُوع ነው፥ ኹሹዕ ያለው በሶላት ላይ የሚቆም የአሏህ ባሪያ "ኻሺዕ" خَاشِع ይባላል፦

ቁርኣን 2፥45 በትእግስት እና በሶላትም ተረዱ! እርሷም ሶላት በ-"ፈሪዎች" ላይ እንጂ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡
وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ
ቁርኣን 23፥2 እነዚያ እነርሱ በሶላታቸው ውስጥ አሏህን "ፈሪዎች" የሆኑት፡፡
الَّذِينَ هُمْ فِي صَلَاتِهِمْ خَاشِعُونَ

እነዚህ አናቀጽ ላይ "ፈሪዎች" ለሚለው የገባው ቃል "ኻሺዒን" خَاشِعِين ሲሆን "ትሁታን" "ተናናሾች" "ተዋራጆች" ማለት ነው፥ ሶላት ላይ ለመቆም ቀላል የሚያደርገው ለአሏህ መተናነስን፣ መጎባደድን፣ ዝቅ ማድረግን፣ መዋረድን ነው። መተናነስ ለአሏህ ተብሎ የሚደረግ ዒባደቱል ቀልቢያ ነው፦

ቁርኣን 7፥55 ጌታችሁን "ተዋርዳችሁ" በድብቅም ለምኑት፡፡
ادْعُوا رَبَّكُمْ تَضَرُّعًا وَخُفْيَةً
ቁርኣን 2፥150 አትፍሩዋቸውም፤ ፍሩኝም።
فَلَا تَخْشَوْهُمْ وَاخْشَوْنِي

አምላካችን አሏህ "ኢኽሸውኒ" خْشَوْنِي ማለቱ በራሱ መተናነስ የአምልኮ ክፍል መሆኑን ያሳያል። መተናነስ ከትህትና ወደ ልዕልና፣ ከዕርደት ወደ ዕርገት፣ ከቀንበር ወደ መንበር አሸጋግሮ ለጀነት የሚያስበስር ነው፦

ቁርኣን 22፥34 ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡
وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ
ቁርኣን 21፥90 ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡
وَكَانُوا لَنَا خَاشِعِينَ

ሌላው ለሰው የምንተናነሰው መተናነስ ትህትና ሲሆን "ኸፍድ" ነው፥ "ኸፍድ" خَفْض የሚለው ቃል "ኸፈደ" خَفَضَ ማለትም "ዝቅ አለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዝቅታ"lowliness" ማለት ነው፦

ቁርኣን 17፥24 ለሁለቱም(ለወላጆች) ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፡፡
وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ
ቁርኣን 26፥215 ከምእምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ፡፡
وَاخْفِضْ جَنَاحَكَ لِمَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ

እነዚህ አናቀጽ ላይ "ዝቅ አርግ" ለሚለው የገባው ትእዛዛዊ ግሥ "ኢኽፊድ" اخْفِضْ ነው፥ ኸፍድ የተዋዱዕ ክፍል ነው፦

ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 123
ዒያድ ኢብኑ ሒማር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ወደ እኔ፦ "ተናነሱ፣ አንዱ ሌላውን አይጨቁን፣ አንዱ በሌላው ላይ አይኩራ"የሚለውን ገልጧል"። عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ، أَنَّهُ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ أَوْحَى إِلَىَّ أَنْ تَوَاضَعُوا حَتَّى لاَ يَبْغِيَ أَحَدٌ عَلَى أَحَدٍ وَلاَ يَفْخَرَ أَحَدٌ عَلَى أَحَدٍ ‏"‏ ‏.‏

አምላካችን አሏህ በተዋዱዕ ኻሺዒን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም