በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
ቁርኣን 4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡
وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ
"ሥላሴ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሠለሠ" ማለትም "ሦስት አደረገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሦስትነት" ማለት ነው፥ የስም መደቡ ደግሞ "ሥሉስ" ማለትም "ሦስት" ማለት ነው። የብሉይ ኪዳን ነቢያት ግልጠተ መለኮት የሚመጣላቸው የነበረው በዕብራይስጥ ወይም በዐረማይስጥ እንጂ በግዕዝ አልነበረም፥ ነገር ግን በ 1980 ዕትም በታተመው በ ሰማንያ አሐዱ"81" ቀኖና ላይ "ሥላሴ" የሚለውን ቃል እንደተጠቀሙ በማስመሰል በአምስት መጻሕፍት ውስጥ 14 ቦታ ቀስጠውታል፦
- መጽሐፈ ሲራክ 44፥10 መጽሐፈ ሲራክ 39፥21 መጽሐፈ ሲራክ 15፥17 መጽሐፈ ሲራክ 3፥22
- መጽሐፈ ጥበብ 17፥10 መጽሐፈ ጥበብ 6፥6
- መጽሐፈ ዮዲት 11፥19
- መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል 12፥48 መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል 4፥5
- መጽሐፈ ሄኖክ 38፥10 መጽሐፈ ሄኖክ 17፥17 መጽሐፈ ሄኖክ 13፥14 መጽሐፈ ሄኖክ 6፥24 መጽሐፈ ሄኖክ 5፥38
ለናሙና ያክል ይህንን ተመልከቱ፦
መጽሐፈ ሲራክ 3፥22 "ሥላሴ" ከሰው ይልቅ የገለጡልህ ምሥጢር የለምና ከግብር ገብተህ ባሕርየ ሥላሴን አትመራመር።
አምስቱ መጻሕፍት ውስጥ ያለውን ንግግር ተናገሩት የተባሉት ነቢያት የተናገሩበት ቋንቋ በሥረ መሠረት"orgin" ስለሌለ እውነታውን ማመሳከር ባይቻልም ቅሉ ግን ግዕዙ ላይ በአምስት መጻሕፍት ውስጥ 14 ቦታ "ሥላሴ" የሚለው ቃል የለም፥ ይህንን የተረዱት ሰዎች በ 2000 ዕትም በታተመው በ ሰማንያ አሐዱ ቀኖና ውስጥ የተቀሰቱትን ቅሰጣ አሽቀንጥረው አውጥተውታል። ለናሙና ያክል ይህንን ተመልከቱ፦
መጽሐፈ ሲራክ 3፥22 አላስፈላጊ ሥራዎችን አትመራመር፤ ከሰዎች ይልቅ ለአንተ እጅግ ተገልጦልሃና።
ስለዚህ "ሥላሴ" የሚለው ቃል ባይብል ላይ የለም" ለሚለው እውነታ ሐቁን በመግለጥ ስትቀስጡ የነበረው ሥላሴአዊ ቅሰጣ እናጋልጣለን። ወሰን አልፋችሁ «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
ቁርኣን 4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡
وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ
አሏህ ለእናንተ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም