በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
ቁርኣን 88፥17 "ከሓዲዎች አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!"።
أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ
አምላካችን አሏህ "ግመል" የሚለው ቃል በቁርኣን ናቃህ፣ ኢቢል፣ ጀመል፣ ሪካብ ወዘተ በሚል በተለያዩ ቃላት አምጥቶታል፥ ለምሳሌ፦
"ናቃህ"
"ናቃህ" نَاقَة ማለት "ሴት ግመል" ማለት ሲሆን በተአምር የተገኘች ግመል ናት፦
ቁርኣን 91፥13 "ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ ሷሊህ፦ «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም ተጠንቀቁ» አላቸው"፡፡
فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ نَاقَةَ اللَّهِ وَسُقْيَاهَا
"ኢቢል"
"ኢቢል" إِبِل ማለት "ሴት ግመል" ማለት ሲሆን ጥቅላዊ ሴት ግመል ናት፦
ቁርኣን 88፥17 "ከሓዲዎች አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!"።
أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ
"ጀመል"
"ጀመል" جَمَل ማለት "ግመል" ማለት ሲሆን አጠቃላይ ግመልን ለማመልከት የመጣ ነው፦
ቁርኣን 7፥40 "እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም፡፡ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ ገነትን አይገቡም፡፡ እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን"፡፡
إِنَّ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَاسْتَكْبَرُوا عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ وَلَا يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ الْجَمَلُ فِي سَمِّ الْخِيَاطِ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُجْرِمِينَ
"ሪካብ"
"ሪካብ" رِكَاب ማለት "ግመል" ማለት ሲሆን ልክ እንደ ጀመል አጠቃላይ ግመልን ለማመልከት የመጣ ነው፦
ቁርኣን 59፥6 "ከእነርሱም ገንዘብ በመልእክተኛው ላይ አላህ የመለሰው በእርሱ ላይ ፈረሶችን እና "ግመሎችን" አላስጋለባችሁበትም፡፡ ግን አላህ መልክተኞቹን በሚሻው ሰው ላይ ይሾማል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው"፡፡
وَمَا أَفَاءَ اللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِ مِنْهُمْ فَمَا أَوْجَفْتُمْ عَلَيْهِ مِنْ خَيْلٍ وَلَا رِكَابٍ وَلَـٰكِنَّ اللَّهَ يُسَلِّطُ رُسُلَهُ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
"በደናህ"
"በደናህ" بَدَنة ሲሆን የበደናህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ቡድን" بُدْن ነው፥ ይህም ለእርድ የሚሆን የግመል ጊደር ነው፦
ቁርኣን 22፥36 "ግመሎችንም ለእናንተ ከአላህ ሃይማኖት ምልክቶች አደረግናቸው"፡፡
وَالْبُدْنَ جَعَلْنَاهَا لَكُم مِّن شَعَائِرِ اللَّهِ لَكُمْ
"ዒሻር"
"ዒሻር" عِشَار ማለት "እርጉዝ ግመል" ማለት ነው፦
ቁርኣን 81፥4 "የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም ያለጠባቂ በተተዉ ጊዜ"።
وَإِذَا الْعِشَارُ عُطِّلَتْ
"ሂም"
"ሂም" هِيمِ ማለት "የተጠማ ግመል" ማለት ነው፦
ቁርኣን 56፥55 «የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡»
فَشَارِبُونَ شُرْبَ الْهِيمِ
"በዒር"
"በዒር" بَعِير ማለት "መጫኛ ግመል" ነው፦
ቁርኣን 12፥72 «የንጉሡ መስፈሪያ ጠፍቶናል፡፡ እርሱንም ላመጣ ሰው የግመል ጭነት አለው፡፡ እኔም በእርሱ ተያዥ ነኝ» አለ"፡፡ قَالُوا نَفْقِدُ صُوَاعَ الْمَلِكِ وَلِمَن جَاءَ بِهِ حِمْلُ بَعِيرٍ وَأَنَا بِهِ زَعِيمٌ
"ዷሚር"
"ዷሚር" ضَامِر ማለት "ከሲታ ግመል" ማለት ነው፦
ቁርኣን 22፥27 "በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና" አልነው"፡፡
وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ
አምላካችን አሏህ ቁርኣንን ከሚያስተነትኑ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም