በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ቁርኣን 50፥7 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት፡፡ "በውስጧም ከሚያስደስት ጥንድን ሁሉ አበቀልን"፡፡
وَالْأَرْضَ مَدَدْنَاهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ

"ዘውጅ” زَوْج የሚለው ቃል “ጥንድ” “ባል” ወይም “ሚስት” ተብሎ ተቀምጧል፦

ቁርኣን 58:1 አላህ የዚያችን በባልዋ ነገር የምትከራከርህንና ወደአላህ የምታስሙተውን ቃል በእርግጥ ሰማ።
قَدْ سَمِعَ ٱللَّهُ قَوْلَ ٱلَّتِى تُجَٰدِلُكَ فِى زَوْجِهَا وَتَشْتَكِىٓ إِلَى ٱللَّهِ وَٱللَّهُ يَسْمَعُ تَحَاوُرَكُمَآ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌۢ بَصِيرٌ
ቁርኣን 7:19 አዳምም ሆይ! አንተም ሚስትህም ከገነት ተቀመጡ፤
وَيَٰٓـَٔادَمُ ٱسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ ٱلْجَنَّةَ فَكُلَا مِنْ حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
ቁርኣን 35:11 አላህም ከዐፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ጥንዶች አደረጋችሁ
وَٱللَّهُ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍۢ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍۢ ثُمَّ جَعَلَكُمْ أَزْوَٰجًۭا
ቁርኣን 53:45 እርሱም ሁለቱን ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን ፈጠረ
وَأَنَّهُۥ خَلَقَ ٱلزَّوْجَيْنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلْأُنثَىٰ

“ዘውጀይኒ” زَّوْجَيْنِ ሙተና ሲሆን ሁለት የወንድ እና የሴት ዓይነቶች በሚል መጥቷል፤ “ባልዋ” ለሚለው ቃል የገባው “ዘውጂሃ” زَوْجِهَا መሆኑ እና “ሚስትህ” ለሚለው ቃል የገባው ደግሞ “ዘውጅከ” َزَوْجُكَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አላህ ለእኛ ከምድር ጥንድ ጥንድ የሆኑ ፍጥረታትን ፈጥሮልናል፦

ቁርኣን 50፥7 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት፡፡ "በውስጧም ከሚያስደስት ጥንድን ሁሉ አበቀልን"፡፡
وَالْأَرْضَ مَدَدْنَاهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዓይነት" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዘውጅ” زَوْج ሲሆን “ጥንድ” ማለት ነው። ለእኛ የተፈጠሩት እነዚህም ጥንድ ጥንድ የሆኑ ፍጥረታት እንስሳት እና ዕፅዋት ናቸው። እስቲ ይህንን እሳቤ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"እንስሳት"

እንስሳት ከምድር የተፈጠሩ መነሻቸው ውኃ የሆኑ ፍጥረታት ናቸው፦

ቁርኣን 24፥45 "አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ፡፡ ከእነርሱም በሆዱ ላይ የሚኼድ አለ፤ ከእነሱም በሁለት እግሮች ላይ የሚኼድ አለ፡፡ አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል"፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡
وَاللَّهُ خَلَقَ كُلَّ دَابَّةٍ مِّن مَّاءٍ ۖ فَمِنْهُم مَّن يَمْشِي عَلَىٰ بَطْنِهِ وَمِنْهُم مَّن يَمْشِي عَلَىٰ رِجْلَيْنِ وَمِنْهُم مَّن يَمْشِي عَلَىٰ أَرْبَعٍ ۚ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
ቁርኣን 42፥11 ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፡፡ ከራሳችሁ ጥንዶችን፣ ከቤት እንስሳዎችም ጥንዶችን ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ በእርሱ ያበዛችኋል፡፡ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡
فَاطِرُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا وَمِنَ الْأَنْعَامِ أَزْوَاجًا ۖ يَذْرَؤُكُمْ فِيهِ ۚ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

"ከቤት እንስሳዎችም ጥንዶችን ለእናንተ አደረገላችሁ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። አሁንም “አዝዋጅ” أَزْوَاج ተብሎ የተቀመጠው ቃል ” ዘውጅ” زَوْج ለሚለው ቃል ብዜት ሲሆን “ጥንዶች” ማለት ነው፤ እንስሳት የጾታ ጥንዶች እንደሆኑም እሙንና ቅቡል ነው። በእነዚህ እንስሳ ላይ ሰው ባለቤት እና ንጉሥ ነው፦

ቁርኣን 36፥71 እኛ እጆቻችን ከሠሩት "ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው"፡፡
أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَا أَنْعَامًا فَهُمْ لَهَا مَالِكُونَ

“ባለ መብት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ማሊክ” مَٰلِك ማለትም “ባለቤት”owner” ማለት ሲሆን ሚምን በሁለት ሃረካት ሲሳብ ሚም ፈትሃ አሊፍ ስኩን “ማ” مَٰ ብሎ ሲቀራው “ባለቤት”owner” ይሆናል፤ እንዲሁ “መሊክ”مَلِيك ብሎ ሚምን ባለ አንድ ሃረካ ተስቦ ሚም ፈትሃ “መ” ብሎ مَ ሲቀራ “ንጉሥ”king” ይሆናል። ወደ ነጥቡ ስንገባ ሰው የእንስሳት "ንጉሥ" "ባለቤት" "ባለመብት" መሆኑን ነው።

ነጥብ ሁለት
"ዕፅዋት"

ዕፅዋትም ከምድር የተፈጠሩ መነሻቸው ውኃ የሆኑ ፍጥረታት ናቸው፦

ቁርኣን 50፥9 "ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን፡፡ በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን ፍሬ አበቀልን"፡፡
وَنَزَّلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً مُّبَارَكًا فَأَنبَتْنَا بِهِ جَنَّاتٍ وَحَبَّ الْحَصِيدِ
ቁርኣን 15፥19 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልናባት፡፡ "በውስጧም የተለካን በቃይ ሁሉ አበቀልንባት"፡፡
وَالْأَرْضَ مَدَدْنَاهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ شَيْءٍ مَّوْزُونٍ

ዕፅዋት ልክ እንደ እንስሳት የተባእት እና የእንስት ህዋስ"gamete" ያመነጫሉ። አላህ በዕፅዋት መካከል ጥንድ የሆኑ ተቃራኒ ጾታዎች እንዳሉ ለማመልከት “ዘውጀይኒ” زَوْجَيْنِ በማለት ይናገራል፦

ቁርኣን 13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ፡፡
وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

“ኩል” كُلٌّ ማለትም “ሁሉ” የሚለው ቃል ፍጹማዊ “Absolute" ሆኖ ሲመጣ “ሙጥለቅ” مطلق ሲባል በአንጻራዊ “Relative” ሆኖ ሲመጣ ደግሞ "ቀሪብ” قريب ይባላል። እዚህ አንቀጽ ላይ ቀሪብ ሆኖ የመጣ ነው። ነቢያችን"ﷺ" በተላኩበት ጊዜ ላይ ዕፅዋት ጾታ አላቸው ብሎ ማንም ሰው ዐያውቅም ነበር፥ በዚህ ጊዜ አምላካችን አላህ ሁሉን ዐዋቂ በመሆኑ “ዘውጀይኒ” በማለት ዕፅዋት ጥንዶች እንደሆኑ ነግሮናል። በተጨማሪም ይህንንም እሳቤ ቁርኣን በወረደበት ጊዜ ዐለማወቃችንንም ለማመልከት፦ "ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው" በማለት በሦስተኛ መደብ እራሱ ይናገራል፦

ቁርኣን 36፥36 ያ ምድር ከምታበቅለው ከራሶቻቸውም ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው፡፡
سُبْحَانَ الَّذِي خَلَقَ الْأَزْوَاجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنبِتُ الْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ

አምላካችን አላህ ጊዜው ሲደርስ በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራት ይሆን ዘንድ ዕፅዋት ጾታ እንዳላቸው ዐሳውቆናል። "ጋይኒ" γυνή ማለት "ሴቴ" ማለት ሲሆን ይህቺ የዕፅዋት እንቁላል ህዋስ"gynoecious" በሥነ-ሕይወት ጥናት "ካርፔልስ"carpels" ትባላለች፥ "አንድሮ" ἀνήρ ማለት "ወንዴ" ማለት ሲሆን የዕፅዋት የዘር ህዋስ"Androecium" በሥነ-ሕይወት ጥናት "ስቴመንስ"stamens" ይባላል።

እንግዲህ እንስሳት እና ዕፅዋት ከምድር የተፈጠሩ መነሻቸው ውኃ የሆኑ ፍጥረታት መሆናቸውን ካየን ዘንዳ የተፈጠሩበት አላማ ለሰው መደሰቻ ነው፦

ቁርኣን 2፥29 "እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው"፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا
ቁርኣን 50፥7 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት፡፡ "በውስጧም ከሚያስደስት ጥንድን ሁሉ አበቀልን"፡፡ وَالْأَرْضَ مَدَدْنَاهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ

በባይብልም ከሄድን እንስሳት እና ዕፅዋት ከምድር የተፈጠሩ መነሻቸው ውኃ የሆኑ ፍጥረታት መሆናቸውን ይናገራል፦

ዘፍጥረት 1፥20 እግዚአብሔርም አለ፦ "ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ"
ዘፍጥረት 1፥24 እግዚአብሔርም አለ፦ "ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ! እንዲሁም ሆነ"
መክብብ 3፥19-20 "የሰው ልጆች እና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው"፤ ድርሻቸውም ትክክል ነው፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው፤ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም። ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፤ "ሁሉ ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል"
ዘፍጥረት 1፥11 እግዚአብሔርም፦ "ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል! አለ፤ እንዲሁም ሆነ"

✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም