በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ቁርኣን 21፥22 በሁለቱ (በሰማያትና በምድር) ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡
لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

በሄለናዊ ግሪክ ሥነ-ተረት"hellenistic Greek mythology" ስለ አማልክት ያላቸው እሳቦት በሦስት ይከፈላል፥ አንደኛ አባት የሆነ አምላክ፣ ሁለተኛ ልጅ የሆነ አምላክ እና ሦስተኛ መንፈስ የሆነ አምላክ ነው።
"ቴዎስ" θεός ማለት በግሪክ ኮይኔ "አምላክ" ማለት ነው፥ የቴዎስ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ቴዎኢ" Θεοί ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው። "ዘዩስ" Ζεύς የአማልክት ንጉሥ፣ የሰማዩ አባት ሲሆን ማዕረጉ "ፓተር" πατήρ ማለትም "አባት" ነው፥ "ቴዎ ፓተር" Θεῷ πατήρ ማለት "አምላክ አባት"God the father" ማለት ነው።

"ሄሚሱስ" ἥμισυς ማለት "ከፊል"demi" ማለት ሲሆን "ሄሚቴዎስ" ἡμιθεός" ማለት "ከፊል አምላክ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ "ሄራክለስ" Ἡρακλῆς የተባለው አምላክ ከዘይዩስ የተገኘ የዘዩስ ልጅ ሲሆን ማዕረጉ "ሁዮስ" υἱός ማለትም "ልጅ" ነው። "ቴዎ ሁዮስ" Θεῷ υἱός ማለት "አምላክ ልጅ"God the son" ማለት ነው። ሄራክለስ አምላክ ከሆነው ከአባቱ ከዘዩስ ስለተወለደ አምላክ ቢሆንም ሰው ከሆነችው ከእናቱ "አልክሜኔ" Ἀλκμήνη ከተባለች ሴት ሰው ስለተገኘ ሰው ነው፥ አምላክ እና ሰው በአንድ ማንነት"hypostatic union" ያለ ነው።

"ዳይሞን" δαίμων ማለት በግሪክ ኮይኔ "አምላክ" ማለት ነው፥ የዳይሞን ብዙ ቁጥር ደግሞ "ዳይሞንዮን" δαιμονίων ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥18 "አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል" Ξένων δαιμονίων δοκεῖ καταγγελεὺς εἶναι·

ኢስጦኢኮች ከተባሉት ፈላስፎች "አማልክት" ለሚለው የተጠቀሙበት ቃል "ዳይሞንዮን" δαιμονίων እንደሆነ ልብ አድርግ!
"አጋቶስ" ἀγαθός ማለት "ቅዱስ" "ሰናይ" "መልካም" "ጥሩ" "ደግ" ማለት ነው፥ "አጋቶዳይሞን" ἀγαθοδαίμων ማለት "ቅዱስ አምላክ" ማለት ነው።
"ካኮስ" κακός ማለት "ርኩስ" "እኩይ" "መጥፎ" "ክፉ" "ከይሲ" ማለት ነው፥ "ካኮዳይሞን" κακοδαίμων ማለት "ርኩስ አምላክ" ማለት ነው።
"ፕኒውማ" πνεῦμα ማለት "መንፈስ" ማለት ነው፥ የፕኒውማ ብዙ ቁጥር "ፕኒውማታ" πνεύματα ሲሆን "መናፍስት(መንፈሶች) ማለት ነው። ለምሳሌ፦ ከዘንዶውም አፍ፣ ከአውሬው አፍ እና ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ የሚወጡ "የአማልክት መናፍስት" ተብለዋል፦

ራእይ 16፥14 ምልክት እያደረጉ የአማልክት መናፍስት ናቸውና።
εἰσὶν γὰρ πνεύματα δαιμονίων ποιοῦντα σημεῖα,

"አማልክት" ለሚለው የገባው የግሪኩ ቃል "ዳይሞንዮን" δαιμονίων እንደሆነ ልብ አድርግ! እነዚህ ምድባቸው "ካኮዳይሞን" κακοδαίμων ማለትም "ርኩስ አምላክ" ነው፥ "ርኩስ መንፈስ" ወይም "ርኵሳን መናፍስት" በመባል ይታወቃሉ፦

ማቴዎስ 12፥43 "ርኩስ መንፈስ" ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፥ አያገኝምም።
ራእይ 16፥13 ከዘንዶውም አፍ፣ ከአውሬው አፍ እና ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት "ርኵሳን መናፍስት" ሲወጡ አየሁ።

"ቅዱሳን መናፍስት" "ቅዱሳን አማልክት" አለቃቸው "አጋቶዳይሞን" ἀγαθοδαίμων ማለትም "ቅዱስ አምላክ" ሲሆን "ፕኒውማ ሐጊዎን" πνεῦμα ἁγίων ማለትም "ቅዱስ መንፈስ" ይሉታል፥ ይህን "ቴዎ ፕኒውማ ሐጊዎን" Θεῷ πνεῦμα ἁγίων ማለትም "አምላክ መንፈስ ቅዱስ"God the holy Spirit" ይሉታል።

ክርስትና ሦስተኛ ክፍለ ዘመን ላይ በበግሪክ እና በሮም የተጀመረው የአሞኒየስ"Ammonius" እና የተማሪው ፕሎቲኒየስ"Plotinus" ፍልስፍና ተጽዕኖ ላይ ወድቋል፥ የአሞኒየስ እና የተማሪው ፕሎቲኒየስ ፍልስፍና "አዲሱ አፍላጦናዊነት"Neoplatonism" ነው።
በ325 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት የተካሄደው የኒቂያ ጉባኤ ኢየሱስን "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዎስ" Ο Θεός ο γιος ማለትም "እግዚአብሔር ወልድ"God the Son" የሚል የአቋም መግለጫ መስጠቱ እና "ቴዎን ኤክ ቴዉ" Θεὸν ἐκ Θεοῦ ማለትም "ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" ማለቱ የጤና ይሆን?
በ381 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቀዳማይ ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የተካሄደው የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ መንፈስ ቅዱስን "ሆ ቴዎስ ሆ ኑማ ቶ ሐጊዎን" Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ማለትም "እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ"God the Holy Spirit" ማለቱ የጤና ይሆን?

አምላካችን አሏህ ምንም ልጅን አልወለደም፥ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ ኖሮ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፥ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አሏህ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ፦

ቁርኣን 23፥91 አላህ ምንም ልጅን አልወለደም፥ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ ኖሮ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ፡፡
مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ ۚ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَـٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

በሰማያት እና በምድር ውስጥ ከአሏህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፥ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦

ቁርኣን 21፥22 በሁለቱ (በሰማያትና በምድር) ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡
لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም