በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ቁርኣን 5፥77 «እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የኾነን ወሰንን አትለፉ! በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድም የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ» በላቸው፡፡
قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ غَيْرَ الْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوا أَهْوَاءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا كَثِيرًا وَضَلُّوا عَن سَوَاءِ السَّبِيلِ

"ኹራፋህ" خُرَافَة የሚለው ቃል "ኸረፈ" خَرَفَ‎ ማለትም "ተረተ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሥነ-ተረት"mythology" ማለት ነው፥ የኹራፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኹራፋት" خُرَافَات ነው። አይሁዳውያን በጥንት ጊዜ በፋርሳውያን "ሲሙርግ" እየተባለ፣ በሱሜሪያን "አንዙ" እየተባለ፣ በግሪክ ደግሞ "ፊኒክስ" እየተባለ የሚነገርለትን "ዚዝ" זִיז በመጽሐፉ ላይ አስገብተዋል፥ "ዚዝ" የአእዋፋት ንግሥት ስትሆን መኖሪያዋ ሰማይ ላይ ነው። ፀሐይ ምድርን 109 ጊዜ ያክል የምትበልጥ ፍጡር ስትሆን በአይሁዳውያን ሥነ-ተረት "ዚዝ ፀሐይን በክንፏ መጋረድ የምትችል ትልቅ ወፍ ናት፥ ግዝፈቷ እንደ ሌዋታን ስትሆን እንቁላሏ ቢወድቅ አንድ ከተማ ሊያወድም ይችላል" ተብሎ ይታመናል፥ ባይብል ላይም ስለ ዚዝ ይናገራል፦

መዝሙር 80፥13 የሜዳ "ዚዝ" ይበላታል"። וְזִ֖יז שָׂדַ֣י יִרְעֶֽנָּה׃
መዝሙር 50፥11 የሜዳ "ዚዝ" በእኔ ዘንድ ነው። וְזִ֥יז דַ֗י עִמָּדִֽי

"በእኔ ዘንድ" ማለት ሰማይ ላይ ማለት ነው፥ የአእዋፋት አለቃ ዚዝ የአይሁዳውያን አጋዳህ ላይ፦ "ሌዋታን የዓሣዎች ንጉሥ እንደሆነ ሁሉ ዚዝም በወፎች ላይ እንድትገዛ ተሹማለች"።

ይህቺ ጭራቅ ከተፈጠረችበት ጀምራ እስከ አሁን የማትወልድ እና የማትሞት ስትሆን የፍርዱ ቀን ታርዳ ለተመረጡ አትክልታውያን"vegetarian" ምግብ ትሆናለች፥ ይህ የፓጋኑን ሥነ ተረት የመጽሐፉ ሰዎች አይሁዳውያን በመጽሐፎቻቸው አስገብተዋል። የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድም የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ፦

ቁርኣን 5፥77 «እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የኾነን ወሰንን አትለፉ! በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድም የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ» በላቸው፡፡
قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ غَيْرَ الْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوا أَهْوَاءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا كَثِيرًا وَضَلُّوا عَن سَوَاءِ السَّبِيلِ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም