በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ቁርኣን 4፥82 ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ፦
"አሏህ መልእክተኞች እኩል አድርጓል ወይስ አላደረገም?
A. እኩል አድርጓል፦
ቁርኣን 2፥285 "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِ

B. እኩል አላደረገም፦
ቁርኣን 2፥253
"እነዚህን መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን"፡፡ تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ

መልስ፦

ለአይሁዳውያን፦ «አላህም ባወረደው ሁሉ እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በእኛ ላይ በተወረደው ብቻ እናምናለን» ይላሉ፥ "በእኛ ላይ በተወረደው" ለሚሉት ለነቢያት ወሕይ አረጋጋጭ የሆነው ቁርኣን በመካድ በከፊሉ በማመን እና በከፊሉ በመካድ አስተባብለዋል፦

ቁርኣን 2፥91 ለእነርሱ «አላህም ባወረደው ሁሉ እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በእኛ ላይ በተወረደው ብቻ እናምናለን» ይላሉ፥ ከእርሱ በኋላ ያለው እርሱ ከእነርሱ ጋር ላለው አረጋጋጭ እውተኛ ሲኾን ይክዳሉ፡፡
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ آمِنُوا بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ قَالُوا نُؤْمِنُ بِمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَيَكْفُرُونَ بِمَا وَرَاءَهُ وَهُوَ الْحَقُّ مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَهُمْ

አምላካችን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችንን "ቁል" قُلْ በሚል ትእዛዛዊ ግሥ በእርሳቸው ላይ በተወረደው ቁርኣን እና ከእርሳቸው በፊት በነበሩት ነቢያት ላይ በተወረደው ወሕይ "አመንን" እንዲሉ አዟል፦

ቁርኣን 3፥84 በል፦ "በአላህ እና በእኛ ላይ በተወረደው አመንን"
قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا
ቁርኣን 3፥84 "በኢብራሂም፣ በኢስማዒል፣ በኢስሓቅ፣ በያዕቆብ፣ በነገዶችም ላይ በተወረደው፣ ለሙሳሣ እና ለዒሣ በተሰጡት፣ በዚያም ለነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው አመንን"።
وَمَا أُنزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ

አምላካችን አሏህ ለዚያ ነው፦ "መልእክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ" በማለት የነገረን፦

ቁርኣን 2፥285 መልእክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡
آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ

ሌላ አንቀጽ ላይ ደግሞ አምላካችን አሏህ የተወዳጁ ነቢያችን ተከታዮች ምእመናን "ቁሉ" قُولُوا በሚል ትእዛዛዊ ግሥ በእነርሱ ላይ በተወረደው ቁርኣን እና ከእርሳቸው በፊት በነበሩት ነቢያት ላይ በተወረደው ወሕይ "አመንን" እንዲሉ አዟል፦

ቁርኣን 2፥136 በሉ፦ "በአላህ እና ወደ እኛ በተወረደው አመንን"
قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا
ቁርኣን 2፥136 ወደ ኢብራሂም፣ ወደ ኢስማዒል፣ ወደ ኢስሐቅ፣ ወደ ያዕቁብ እና ወደ ነገዶቹም በተወረደው፣ በዚያም ለሙሣ እና ለዒሣ በተሰጡት፣ በዚያም ለነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት አመንን"።
وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ

አምላካችን አሏህ ለዚያ ነው፦ "ምእመናን እንደዚሁ አመኑ" በማለት የነገረን፦

ቁርኣን 2፥285 ምእመናን እንደዚሁ አመኑ፡፡
وَالْمُؤْمِنُونَ

"ሁሉም" ማለትም ተወዳጁ ነቢያችን እና ምእመናን «ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም» የሚሉ ሲኾኑ አመኑ፦

ቁርኣን 2፥285 ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልእክተኞቹም «ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም» የሚሉ ሲኾኑ አመኑ፡፡
كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِ
ቁርኣን 3፥84 "ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም"
نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ
ቁርኣን 2፥136 "ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም"
نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ

በሁሉም ነቢያት ላይ የተወረደው የመልእክቱ ጭብጥ ተውሒድ ስለሆነ ከእነርሱ መካከል አንድንም ሳንለይ እናምናለን፥ "ላ ኢላሀ ኢላ አና" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا የሚለው መገሰጫ ለነቢያችን እና ከእርሳቸው በፊት በነበሩት ነቢያት ላይ የወረደ መገሰጫ ነው፦

ቁርኣን 21፥24 «አስረጃችሁን አምጡ፡፡ ይህ መገሰጫ እኔ ዘንድ ያለው ከእኔ በፊትም የነበረ መገሰጫ ነው» በላቸው፡፡
قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ ۖ هَـٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِيَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِي
ቁርኣን 21፥25 ከአንተ በፊትም፦ "እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጂ ከመልእክተኛ አንድንም አላክንም፡፡
وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

"ዚክር" ذِكْر ማለት "መገሰጫ" ማለት ሲሆን ለሁሉም መልእክተኞች የወረደውን መልእክት ተህሊል ስለሆነ አይሁዳውያን በመልእክተኞቹ መካከል ሳይለዩ ማመን ሲገባቸው በተቃራኒው በመካድ «በከፊሉም እናምናለን በከፊሉም እንክዳለን» የሚሉ እነዚያ በእውነት ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው። ለእነርሱ አዋራጅን ቅጣት አሏህ አዘጋጅቷል፦

ቁርኣን 4፥150 እነዚያ በአላህ እና በመልእክተኞቹ የሚክዱ፣ በአላህ እና በመልእክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉ፣ «በከፊሉም እናምናለን በከፊሉም እንክዳለን» የሚሉ፣ በዚህም መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ እነዚያ በእውነት ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ ለከሓዲዎችም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል፡፡
إِنَّ الَّذِينَ يَكْفُرُونَ بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ وَيُرِيدُونَ أَن يُفَرِّقُوا بَيْنَ اللَّهِ وَرُسُلِهِ وَيَقُولُونَ نُؤْمِنُ بِبَعْضٍ وَنَكْفُرُ بِبَعْضٍ وَيُرِيدُونَ أَن يَتَّخِذُوا بَيْنَ ذَٰلِكَ سَبِيلًا أُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَافِرُونَ حَقًّا ۚ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ عَذَابًا مُّهِينًا

ስለዚህ ከመነሻው "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" ያለው አሏህ ሳይሆን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችን እና ምእመናን እንዲሉ ያዘዘው ትእዛዝ ነው፥ "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" ብለው የሚያምኑት ምእመናን ሆነው ሳለ አሏህ "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" ብሎ እንደተናገረ አርጎ መረዳት ዓረፍተነገሩን ከዐውዱ ማፋታት ነው። "አመነ" آمَنَ እና "አመና" آمَنَّا የሚል ኃይለ ቃል ከአንቀጹ በማውጣት እና የራስን አሳብ መክተት በሥነ አፈታት ጥናት"hermeneutics" ፈቲሆት"exegesis" ሳይሆን ሰጊዎት"eisegesis" ነው።
አሏህ እኛን፦ "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም" "በሉ" ያለበት ምክንያት አይሁዳውያን አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው ማውረዱን በምቀኝነት በመካዳቸው ነው፦

ቁርኣን 2፥90 ነፍሶቻቸውን በእርሱ የሸጡበት ነገር ከፋ! እርሱም አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው፡፡
بِئْسَمَا اشْتَرَوْا بِهِ أَنفُسَهُمْ أَن يَكْفُرُوا بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ بَغْيًا أَن يُنَزِّلَ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ችሮታ" ለሚለው የገባ ቃል "ፈድል" فَضْل ሲሆን ሲሆን "ስጦታ" "ችሮታ" "ጸጋ"Bounty” ማለት ነው፥ ሥርወ-ቃሉ "ፈዶለ" فَضَّلَ ማለትም" ሰጠ" "ቸረ" ነው። አምላካችን አሏህ በሚያወርደው ፈድል መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አብልጧል፦

ቁርኣን 2፥253 እነዚህን መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፡፡ تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ
ቁርኣን 17፥55 ከፊሉንም ነቢያት በከፊሉ ላይ በእርግጥ አበለጥን፡፡
وَلَقَدْ فَضَّلْنَا بَعْضَ النَّبِيِّينَ عَلَىٰ بَعْضٍ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "አበለጥን" ለሚለው የገባ ቃል "ፈዶልና" فَضَّلْنَا መሆኑን ልብ ብለካልን? አንደ መልእክተኛ ጋር የተወረደለት ፈድል ሌላው ጋር ሰለሌለ ከፍሉ በከፊሉ ላይ ይበላለጣሉ፥ ለምሳሌ፦ አሏህ ሙሣን በቀጥታ ሲያናግር ሌላውን በመልአክ ወይም በራእይ በማናገር ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አብልጧል፦

ቁርኣን 2፥253 ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አለ፡፡
مِّنْهُم مَّن كَلَّمَ اللَّهُ
ቁርኣን 4፥164 አላህ ሙሣን ማነጋገርን አነጋገረው፡፡
وَكَلَّمَ اللَّهُ مُوسَىٰ تَكْلِيمًا

ይህ የደረጃ ልዩነት እንጂ የኑባሬ ልዩነት አይደለም። ለምሳሌ፦ አሏህ ለመርየምን ልጅ ለዒሣ ግልጽ ተአምራትን በመስጠት እና በቅዱሱ መንፈስ በማበረታታት አብልጧል፦

ቁርኣን 2፥253 ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሣን ግልጽ ተአምራትን ሰጠነው፥ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡
وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَاتٍ ۚ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ
ቁርኣን 2፥87 የመርየምን ልጅ ዒሣን ግልጽ ተአምራትን ሰጠነው፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡
وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ

ግጭት ማለት አሏህ እኛን፦ "እኩል አርጋችሁ እመኑ" ብሎን በተቃራኒው "አንዱን መልእክተኛ ከሌላው አስብልጡ" ቢለን ወይም አሏህ፦ "መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን" ብሎ "ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል ስንለይ እኩል አርገናል" ቢል ኖሮ ግጭት ነበር። ነገር ግን ቁርኣን የፈጣሪያችን የአሏህ ንግግር ስለሆነ እና የሰው ንግግር ስላልገባበት የእርስ በእርስ ግጭት የለውም፦

ቁርኣን 4፥82 ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡
أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

"ኢኽቲላፍ" اخْتِلَاف ማለት "ግጭት" ማለት ሲሆን ቁርኣን ከአሏህ ዘንድ በግልጠተ መለኮት የመጣ የአሏህ ንግግር ስለሆነ እርስ በእርስ አይጋጭም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛን ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም