በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
ቁርኣን 3፥145 "በአላህ ፈቃድ ቢኾን እንጅ ለማንኛይቱም ነፍስ ልትሞት አይገባትም፥ ጊዜውም ተወስኖ ተጽፏል፡፡
وَمَا كَانَ لِنَفْسٍ أَن تَمُوتَ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ كِتَابًا مُّؤَجَّلًا
በባይብል ፈጣሪ ነገርን ሁሉ በ-"ጊዜ" ውብ አድርጎ ሠርቶታል፥ ከሰማይ በታች ለሆነ ነገር ሁሉ "ጊዜ" አለው። ለመወለድ "ጊዜ" እንዳለው ሁሉ ለመሞትም "ጊዜ" አለው፦
መክብብ 3፥11 ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው።
መክብብ 3፥1 ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።
መክብብ 3፥2 ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው።
የሰውን ሩሕ(መንፈስ) በማውጣት ሰውን የሚያሞት፣ ወደ መቃብር የሚያወርድ እና ከመቃብር የሚያወጣ እራሱ ፈጣሪ ነው፦
1ኛ ሳሙኤል 2፥6 ያህዌህ ያሞታል ያድናልም፤ ወደ መቃብር ያወርዳል ያወጣል።
יְהוָ֖ה מֵמִ֣ית וּמְחַיֶּ֑ה מֹורִ֥יד שְׁאֹ֖ול וַיָּֽעַל׃
ዘዳግም 32፥39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ አሞታለው፥ አድንማለሁ።
רְא֣וּ ׀ עַתָּ֗ה כִּ֣י אֲנִ֤י אֲנִי֙ ה֔וּא וְאֵ֥ין אֱלֹהִ֖ים עִמָּדִ֑י אֲנִ֧י אָמִ֣ית וַאֲחַיֶּ֗ה מָחַ֙צְתִּי֙ וַאֲנִ֣י אֶרְפָּ֔א וְאֵ֥ין מִיָּדִ֖י מַצִּֽיל׃
መዝሙር 104፥29 መንፈሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ።
תֹּסֵ֣ף ר֭וּחָם יִגְוָע֑וּן וְֽאֶל־עֲפָרָ֥ם יְשׁוּבֽוּן׃
በጊዜ የሚያሞት እና ሕያው የሚያደርግ ፈጣሪ እንደሆነ ካየን ዘንዳ ሰው ከፍጥረት በፊት የተወሰኑለት የሕይወት ዕድሜ በመጽሐፍ ተጽፏል፦
መዝሙር 139፥16 ለእኔ የተወሰኑልኝ ዘመናት ገና አንዳቸውም ወደ መኖር ሳይመጡ በመጽሐፍህ ተመዘገቡ። (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
גלמי ראו עיניך ועל ספרך כלם יכתבו ימים יצרו ולא אחד בהם׃
እዚህ አንቀጽ ላይ የአዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ "መጽሐፍ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል በዕብራይስጡ "ሰፈር" סֵפֶר ሲሆን ይህም መጽሐፍ ሰው ወደ መኖር ከመምጣቱ በፊት ተወስኖ የተጻፈበት መጽሐፍ ነው፥ ይህንን የአዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ፦ "የሰው የሕይወት ዘመን በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው፥ "በመጽሐፍህ" የእግዚአብሔር ውሳኔዎች ሁሉ የተጻፉበት የሰማይ መዝገብ ነው" በማለት ያትታል። የ 1954 እትም ደግሞ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ ሳይፈጠሩ በመጽሐፍ እንደተጻፉ ይናገራል፦
መዝሙር 139፥16 የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ
አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ። καὶ ἐπὶ τὸ βιβλίον σου πάντες γραφήσονται· ἡμέρας πλασθήσονται καὶ οὐθεὶς ἐν αὐτοῖς.
እዚህ አንቀጽ ላይ በግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ "መጽሐፍ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ቢብሊዮን" βιβλίον ነው፥ "አንድ ስንኳ ሳይኖር" ማለት "ምንም ነገር ሳይኖር" ማለት ሲሆን ምንም ነገር ሳይፈጠር የሰዎች ዕድሜ በአምላክ መጽሐፍ ተጽፏል። ይህንን ኤጲፋንዮስ በቅዳሴ ላይ፦ "ሁሉ በመጽሐፉ የተጻፈ ነው" በማለት ይናገራል፦
የኤጲፋንዮስ ቅዳሴ 14፥15 "ከእርሱ የሚሰወር የለም፣ ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተገለጠ ነው፣ በዓይኖቹ ፊት ሁሉ የተዘረጋ ነው፣ ሁሉ በመጽሐፉ የተጻፈ ነው"።
ኢየሱስ ሲያስተምር፦ "ወደ ላከኝም እሄዳለሁ" በማለት ስለማረጉ ይናገራል፦
ዮሐንስ 7፥33 ኢየሱስም፦ ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ ወደ ላከኝም እሄዳለሁ።
ዮሐንስ 16፥5 አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።
ኢየሱስ ከማረጉ በፊት ስለማረጉ አስቀድሞ ተወስኖ ተጽፎለት ነበር፦
ሉቃስ 22፥22 የሰው ልጅስ እንደ ተወሰነው ይሄዳል።
ማቴዎስ 26፥24 የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል።
"መወሰን" እና "መጻፍ" ተለዋዋጭ ሆኖ መምጣቱ በራሱ ከፍጥረት አስቀድሞ ተወስኖ የሚጻፍበት መጽሐፍ እንዳለ አመላካች ነው። የሰው ዕድሜ ሁሉ ፍጥረት ሳይኖር በመጽሐፍ ከተጻፈ "ዕድሜህ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር" ወይም "ዕድሜአችሁ እንዲረዝም አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ" የሚለው ቃል ትርጉሙ ግልጽ አይደለም፦
ዘጸአት 20፥12 አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።
ዘዳግም 5፥33 በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም ያህዌህ አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።
ወይ እንደ ኢሥላም አስተምህሮት አጀሉል ሙአለቅ እና አጀሉል ሙሠማ የሚባል ትምህርት ስለሌላችሁ የተጻፈው ዕድሜ እንዴት እንደሚረዝም ግልጽ ትምህርት የላችሁም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።
✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም