በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
ቁርኣን 26፥195 ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ አወረደው፡፡
بِلِسَانٍ عَرَبِيٍّ مُّبِينٍ
የቋንቋዎቻችን መለያየት ከአስደናቂ የአሏህ ተአምራት ነው፥ አምላካችን አሏህ መልእክተኞች ሲልክ በወቅቱ የተወለዱበት ማኅበረሰብ ሊግባቡበት በሚችል ቋንቋ ነው፦
ቁርኣን 30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፤ የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ተአምራቶቹ ነው፡፡
وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَٰنِكُمْ
ቁርኣን 14፥4 ከመልክተኛ ማንኛውንም ለእነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በሕዝቦቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም፡፡
ﻭَﻣَﺂ ﺃَﺭْﺳَﻠْﻨَﺎ ﻣِﻦ ﺭَّﺳُﻮﻝٍ ﺇِﻟَّﺎ ﺑِﻠِﺴَﺎﻥِ ﻗَﻮْﻣِﻪِۦ ﻟِﻴُﺒَﻴِّﻦَ ﻟَﻬُﻢْ ۖ ﻓَﻴُﻀِﻞُّ ﭐﻟﻠَّﻪُ ﻣَﻦ ﻳَﺸَﺂﺀُ ﻭَﻳَﻬْﺪِﻯ ﻣَﻦ ﻳَﺸَﺂﺀُ ۚ ﻭَﻫُﻮَ ﭐﻟْﻌَﺰِﻳﺰُ ﭐﻟْﺤَﻜِﻴﻢُ
"ቀውም" قَوْم ማለት "ህዝብ" ማለት ሲሆን በአንድ አካባቢ ተመሳሳይ ባህል፣ ቋንቋ፣ አኗኗር፣ ታሪክ፣ መንግሥት እና ቦታ ያለው ማኅበረሰብን ያመለክታል፥ ለምሳሌ፦ ሙሣ ነቢይ ሆኖ በተነሳበት ዘመን አሏህ ሙሣን ወደ ሕዝቦቹ "በተአምራት" እንደላከው እና እነዚያም ሕዝቦች ፈርዖን እና ሹማምንቶቹ የሚጠቀልል መሆኑን ለማመልከት ወደ ፈሮዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን” በማለት ይናገራል፦
ቁርኣን 14፥5 ሙሳንም፦ "ሕዝቦችህን" ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አውጣ! የአላህንም ቀኖች አስገንዝባቸው" በማለት "በተአምራታችን" በእርግጥ ላክነው።
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ أَنْ أَخْرِجْ قَوْمَكَ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَذَكِّرْهُم بِأَيَّىٰمِ ٱللَّهِ
ቁርኣን 43፥46 ሙሳንም "በተአምራታችን" ወደ ፈርዖን እና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን። እኔ የአለማት ጌታ መልክተኛ ነኝ አላቸውም።
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦ فَقَالَ إِنِّى رَسُولُ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
እዚህ ድረስ ከተግባባን ዘንድ አምላካችን አሏህ ቁርኣንን ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" አውርዶታል፦
ቁርኣን 26፥195 ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ አወረደው፡፡
بِلِسَانٍ عَرَبِيٍّ مُّبِينٍ
ቁርኣን 13፥37 እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው፡፡
وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا
"ሑክም" حُكْم ማለት "ሕግ" "ፍርድ" "ፍትሕ" ማለት ሲሆን "አሕካም" أَحْكَام ደግሞ "ሕግጋት" ማለት ነው፥ አምስቱ አሕካም ፈርድ፣ ሙሥተሐብ፣ ሙባሕ፣ መክሩህ እና ሐራም ምን እንደሆኑ አሏህ ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ አውርዷል። የቁርኣንን ሰዋስው መሠረት እና ውቅር እንዲሁ ዋልታና ማገር እንድንገነዘብ አሏህ ቁርኣንን ዐረብኛ አርድርጎ አውርዶታል፦
ቁርኣን 43፥3 እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው፡፡
إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
ቁርኣን 12፥2 እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው፡፡
إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
"ትገነዘቡ ዘንድ" ለሚለው የገባው ቃል "ለዐለኩም ተዕቂሉን" لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُون ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ዐቀለ" عَقَلَ ማለትም "ተገነዘበ" "ተረዳ" "ዐወቀ" ነው፥ ለመገንዘብ፣ ለመረዳት፣ ለማወቅ የምታስተነትንበት እእምሮ እራሱ "ዐቅል" عَقْل ይባላል። የቁርኣን የአቀራሩ ስልት የሆኑት ሐረካት፣ ተንዊን፣ መድ፣ ስኩን፣ ተሽዲድ እራሱን የቻለ አምሳያ የሌለው የቁርኣኑ ተአምር ነው፦
ቁርኣን 52፥34 እውነተኞችም ቢኾኑ መሰሉ የኾነን ንግግር ያምጡ፡፡
فَلْيَأْتُوا بِحَدِيثٍ مِّثْلِهِ إِن كَانُوا صَادِقِينَ
ቁርኣኑ እራሱ ችሎ በተጅዊድ ሐረካት፣ ተንዊን፣ መድ፣ ስኩን፣ ተሽዲድ አለው፥ የቁርኣን መሰሉ የኾነን ንግግርን ማንም ማምጣት አይችልም። አምላካችን አሏህ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙፍረዳት በማርባት እና በማባዛት ሶርፍ፣ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙፍረዳት በማብራራት ሉጋህ፣ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙረከባት በዓረፍተ ነገር በማዋቀር ነሕው፣ የቁርኣንን ሑሩፉል ሙረከባት የዓረፍተ ነገሩን መልእክት በመግለጽ በላጋህ በማድረግ መዛባት በሌለበት ዐረብኛ አብራርቶታል፦
ቁርኣን 39፥28 መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን አብራራነው፡፡ ሊጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡
قُرْآنًا عَرَبِيًّا غَيْرَ ذِي عِوَجٍ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
ቁርኣን 41፥3 አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው፡፡
كِتَابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
በዐማርኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ ወዘተ... የምናነባቸው የቁርኣን ትርጉም እንጂ ቁርኣን አይደሉም፥ ትርጉም የመልእክቱ አሳብ የምንረዳበት እንጂ የቁርኣኑን ምጥቀት እና ጥልቀት ያለው አሏህ እራሱ ባወደረበት በግልጹ እና መዛባት በሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ነው። ይህ ከላሙል ዐረቢይ የሆነው ቁርኣን የወረደው ለመላው የሰው ልጆች ሁሉ ነው፦
ቁርኣን 6፥90 «በእርሱ በቁርአን ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፡፡ እርሱ ለዓለማት ግሣጼ እንጅ ሌላ አይደለም» በላቸው፡፡
قُل لَّا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ أَجْرًا ۖ إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرَىٰ لِلْعَالَمِينَ
ቁርኣን ለዓለማት ግሣጼ እንደወረደ በተጨማሪ 68፥52 38፥87 12፥104 81፥27 ላይ ተመልከት!
"ዓለማት" የሚለው ቃል በቁርኣን ሰፊ እና ጠባብ ትርጉም አለው፥ በሰፊ ትርጉሙ "የዐለማቱ ጌታ" በሚል ከመጣ "አጽናፈ ዓለማትን" ያመለክታል፦
ቁርኣን 7፥54 የዓለማት ጌታ አላህ ክብሩ ላቀ፡፡
تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ
"ዓለማት" በጠባብ ትርጉሙ ከመጣ "መላውን የሰው ልጆች ሁሉ" ያመለክታል፦
ቁርኣን 29፥10 አላህ "በዓለማት ልቦች" ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ አይደለምን?
أَوَلَيْسَ اللَّهُ بِأَعْلَمَ بِمَا فِي صُدُورِ الْعَالَمِينَ
በተጨማሪ "ዓለማት" በጠባብ ትርጉሙ "መላውን የሰው ልጆች ሁሉ" እንደሚያመለክት
ቁርኣን 2፥47 3፥33 3፥42 21፥91 29፥15 37፥79 3፥96 21፥107 7፥80 26፥165 ላይ ተመልከት!
ስለዚህ አምላካችን አሏህ ለመላውን የሰው ልጆች ሁሉ መገሰጫ ይሆን ዘንድ ቁርኣንን ግልጽ በሆነ ዐረብኛ አውርዶታል።
ቁርኣን ለኦሮሞ በኦሮምኛ፣ ለትግሬ በትግርኛ፣ ለዐማራ በዐማርኛ ስላልወረደ እና በዐረቢኛ ስለወረደ "ለዐረቦች ብቻ ወረደ" ካልን በዓለም ላይ 7,117 ቋንቋዎች ስላሉ ለ 7,117 ቋንቋዎች ተናጋሪዎች በራሳቸው 7,117 ቁርኣኖች እና ነቢያት መላክ ነበረባቸውን? ይህ ሕፀፃዊ አስተሳሰብ ነው፥ አምላካችን አሏህ ለሁሉም የሰው ልጆች አንድ ሰው መርጦ ነቢያችንን"ﷺ" ነቢይ እንዳደረገ ሁሉ እሳቸው የመጡበትን ቋንቋ ዐረብኛን መርጦ መልእክቱን አውርዶበታል። አሏህ ቁርኣንን በነቢያች"ﷺ" ቋንቋ ያገራው የመልእክቱ ጥልቀት እና ምጥቀት እንድንገነዘብ ብቻ ነው፦
ቁርኣን 3፥74 በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡
يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ
ቁርኣን 44፥58 ቁርኣንን በቋንቋህም ያገራነው ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡
فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
ቁርኣን 42፥7 እንደዚሁም የከተሞችን እናት እና በዙሪያዋ ያሉትን ሰዎች ልታስጠነቅቅ እና የመሰብሰቢያውን ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን፡፡
وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّتُنذِرَ أُمَّ الْقُرَىٰ وَمَنْ حَوْلَهَا وَتُنذِرَ يَوْمَ الْجَمْعِ لَا رَيْبَ فِيهِ
"መን ሐውለ-ሃ" مَنْ حَوْلَهَا ማለት "በዙሪያዋ ያሉት ሰዎች" ማለት ሲሆን ቁርኣን ማስጠንቀቂያ ሆኖ የወረደው የከተሞችን እናት የሆነችውን መካን ብቻ ሳይሆን በዙሪያ ያሉትን መላው ሰዎችን ሁሉ ነው፥ "ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን" ማለቱ ደግሞ ቁርኣን ለመላው የሰው ዘር ሁሉ በዐረብኛ መውረዱን ያሳያል። አምላካችን አሏህ የቁርኣንን ጥልቀት እና ምጥቀት የምንገነዘብ ያድርገን! አሚን።
✍ ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም