ጳውሎስ፦ "ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፥ ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው" ይለናል፦
ገላትያ 3፥11-12 ""ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና"".. ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም ""በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው""።
በተቃራኒው ያዕቆብ፦ "ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ" ይለናል፦
ያዕቆብ 2፥24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።
ስለዚህ ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ስለሆኑ በእግዚአብሔር ፊት በሕግ ሥራ ማንም አይጸድቅም ጳውሎስ ሲለን፥ ያዕቆብ ደግሞ ሰው በሕግ ሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ ይለናል። ይህንን ግጭት ለማስቀረት የአትናቴዎስ እና የማርቲን ሉተር የቀኖና መጽሐፍት ውስጥ የያዕቆብ መልእክት አይካተትም።
የቱ ነው ትክክል? "ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው" የሚለው ጳውሎስ ወይስ "ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ" የሚለው ያዕቆብ?
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom