በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 21፥57 «በአላህም እምላለሁ ዟሪዎች ኾናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን አሴራባቸዋለሁ» አለ፡፡
وَتَٱللَّهِ لَأَكِيدَنَّ أَصْنَٰمَكُم بَعْدَ أَن تُوَلُّوا۟ مُدْبِرِينَ
“ጧጉት” طَّٰغُوت የሚለው ቃል “ጦጋ” طَغَىٰ ማለትም “ወሰን አለፈ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “በአሏህ ሐቅ ላይ ወሰን ማለፍ” ማለት ነው፥ በአሏህ ሐቅ ላይ ወሰን ማሳለፊያ ምንነት “ጣዖት” ይባላል። በአሏህ ሐቅ ላይ ወሰን ማሳለፊያ ምንነት "አስናም" እና "አውሳን" ናቸው፥ “አስናም” أَصْنَام ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሠርቶ አምልኮ የሚቀርብለት ጣዖት ሲሆን “አውሳን” أَوْثَٰن ደግሞ ከድንጋይ ተቀርፆ አምልኮ የሚቀርብለት ምንነት ነው። ኢብራሂም ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ ስለ አውሳን፦ "ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት? ብሎ ጠየቃቸው፥ እነርሱም፦ "አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ኾነው አገኘን" አሉ፦
ቁርኣን 21፥52 ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ፦ «ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት» ባለ ጊዜ መራነው፡፡
إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا هَٰذِهِ ٱلتَّمَاثِيلُ ٱلَّتِىٓ أَنتُمْ لَهَا عَٰكِفُونَ
ቁርኣን 21፥53 «አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ኾነው አገኘን» አሉት፡፡
قَالُوا۟ وَجَدْنَآ ءَابَآءَنَا لَهَا عَٰبِدِينَ
እርሱም፦ "እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ" አላቸው፥ እነርሱም፦ "በምሩ መጣህልን ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ? አሉት፦
ቁርኣን 21፥54 «እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ» አላቸው፡፡
قَالَ لَقَدْ كُنتُمْ أَنتُمْ وَآبَاؤُكُمْ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ
ቁርኣን 21፥55 «በምሩ መጣህልን ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ» አሉት፡፡
قَالُوا أَجِئْتَنَا بِالْحَقِّ أَمْ أَنتَ مِنَ اللَّاعِبِينَ
እርሱም፦ “አይደለም ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው፡፡ እኔም በዚህ ላይ ከመስካሪዎቹ ነኝ” አላቸው፦
ቁርኣን 21፥56 «አይደለም ጌታችሁ የሰማያት እና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው፡፡ እኔም በዚህ ላይ ከመስካሪዎቹ ነኝ» አለ፡፡
قَالَ بَل رَّبُّكُمْ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ٱلَّذِى فَطَرَهُنَّ وَأَنَا۠ عَلَىٰ ذَٰلِكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ
ቁርኣን 21፥57 «በአላህም እምላለሁ ዟሪዎች ኾናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን አሴራባቸዋለሁ» አለ፡፡
وَتَٱللَّهِ لَأَكِيدَنَّ أَصْنَٰمَكُم بَعْدَ أَن تُوَلُّوا۟ مُدْبِرِينَ
"አኪደነ" أَكِيدَنَّ ማለት "አደባለው" "አሴራለው" ማለት ነው፥ "ከይድ" كَيْد የሚለው ቃል "ካደ" كَادَ ማለትም "አደበ" "አሴረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ደባ" "ሴራ" ማለት ነው። ይህም ሴራ ዘወር ሲሉ ለእነርሱ የኾነ አንድ ታላቅ ጣዖት ብቻ ሲቀር ስብርብሮችም አደረጋቸው፦
ቁርኣን 21፥58 ዘወር ሲሉ ለእነርሱ የኾነ አንድ ታላቅ ጣዖት ብቻ ሲቀር ስብርብሮችም አደረጋቸው፥ ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እርሱን ተወው፡፡
فَجَعَلَهُمْ جُذَٰذًا إِلَّا كَبِيرًۭا لَّهُمْ لَعَلَّهُمْ إِلَيْهِ يَرْجِعُونَ
አንድ ታላቅ ጣዖት ብቻ ያስቀረው ወደ ታላቁ ጣዖት ተመልሰው የተሰባበሩት ማን እንደሰባበራቸው ሲጠይቁት መልስ ይሰጡ እንደሆነ ዘንድ ነው፥ እነርሱም ጣዖቶቻቸው ተሰባብረው ሲያዩ፦ "በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራ ማነው እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው? ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራህ አንተ ነህን? አሉት፦
ቁርኣን 21፥59 «በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራ ማነው እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው» አሉ፡፡
قَالُوا مَن فَعَلَ هَـٰذَا بِآلِهَتِنَا إِنَّهُ لَمِنَ الظَّالِمِينَ
ቁርኣን 21፥62 «ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራህ አንተ ነህን?» አሉት፡፡
قَالُوا أَأَنتَ فَعَلْتَ هَـٰذَا بِآلِهَتِنَا يَا إِبْرَاهِيمُ
እርሱም፦ "አይደለም ይህ ታላቃቸው ሠራው፡፡ ይናገሩም እንደ ኾነ ጠይቋቸው" አለ፦
ቁርኣን 21፥63 «አይደለም ይህ ታላቃቸው ሠራው፡፡ ይናገሩም እንደ ኾነ ጠይቋቸው» አለ፡፡
قَالَ بَلْ فَعَلَهُۥ كَبِيرُهُمْ هَٰذَا فَسْـَٔلُوهُمْ إِن كَانُوا۟ يَنطِقُونَ
ቁርኣን 21፥64 ወደ እራሳቸውም ተመለሱ፥ «እናንተ በመጠየቃችሁ በዳዮቹ እናንተው ናችሁም» ተባባሉ፡፡
فَرَجَعُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ فَقَالُوٓا۟ إِنَّكُمْ أَنتُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
ቁርኣን 21፥65 ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡ፡፡ «እነዚህ የሚናገሩ አለመኾናቸውን በእርግጥ ዐውቀሃል» አሉ፡፡
ثُمَّ نُكِسُوا۟ عَلَىٰ رُءُوسِهِمْ لَقَدْ عَلِمْتَ مَا هَٰٓؤُلَآءِ يَنطِقُونَ
የእነርሱ ከንቱ አምልኮ የሚያሳፍር ሲሆን የኢብራሂም ሂክማህ ግን ድንቅ ነው፥ በሴራው ሰበረ የተባለው ታላቁ ጣዖት ሆነ ተሰበሩ የተባሉት ጣዖታት የማይናገሩ፣ የማይሰሙ፣ የማያዩ፣ የማይጠቅሙ ነበሩ፦
ቁርኣን21፥66 «ታዲያ ለእናንተ ምንም የማይጠቅማችሁን እና የማይጎዳችሁን ነገር ከአላህ ሌላ ታመልካላችሁን?» አላቸው፡፡
قَالَ أَفَتَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمْ شَيْـًۭٔا وَلَا يَضُرُّكُمْ
አምልኮ የሚገባው ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ሰሚ፣ ሁሉን ተመልካች፣ በግልጠት የሚናገር፣ በጀነት የሚጠቅም፣ በቅጣት የሚጎዳ የዓለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ ነው፥ ይህንን አንዱን አምላክ በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው።
✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም