በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን "አንጻባራቂ" ጨረቃንም "አብሪ" ያደረገ ነው፡፡
هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ
"ሢራጅ" سِرَاج ማለት በዓይን ለማየት አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳ "አንጸባራቂ" ማለት ሲሆን "ሙኒር" مُّنِير ማለት ደግሞ "አብሪ" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ በቅርቢቱ ሰማይ ላይ "ሢራጅ" سِرَاج የተባለችው ፀሐይ እና "ሙኒር" مُّنِير የተባለው ጨረቃ አድርጓል፦
ቁርኣን 10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን ሲራጅ ጨረቃንም ሙኒር ያደረገ ነው፡፡
هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا
አምላካችን አሏህ በቅርቢቱ ሰማይ ላይ ከዋክብትን ያረጋቸው በረጨት ነው፥ “ረጨት” ማለት የከዋክብት ስብስብ”galaxy” ማለት ሲሆን የእኛ ረጨት “ፍኖተ-ሃሊብ”Milky Way” ይባላል። ይህ ረጨት ውፍረቱ 1000 የብርሃን ዓመት እንደሆነ ይገመታል፥ ከአንዱ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ያለው ርቀት በዲያሜትር ሲለካ እንኳን እራሱ 100,000 የብርሃን ዓመት ይሆናል። የሚያጅበው በውስጡ ከ100 እስከ 400 ቢልዮን ከዋክብቶች እንደያዘ ይገመታል፥ ይህ አንዱ ኅብረ-ከዋክብት ወይም ማዛሮት”constellation” ደግሞ “ቡርጅ” بُرْج ይባላል። በቅርቢቱ ሰማይ ብዙ ረጨቶች ስላሉ አምላካችን አሏህ “ቡሩጅ” بُرُوج በማለት ነግሮናል፦
ቁርኣን 37፥6 እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡
إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِبِ
ቁርኣን 25፥61 “ያ በሰማይ ቡሩጆችን ያደረገ እና በእርሷም ፀሐይን ሲራጅ እና ጨረቃን ሙኒር ያደረገ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ”፡፡
تَبَارَكَ الَّذِي جَعَلَ فِي السَّمَاءِ بُرُوجًا وَجَعَلَ فِيهَا سِرَاجًا وَقَمَرًا مُّنِيرًا
"ፊ-ሃ" فِيهَا ማለት "በ-ውስጧ" ማለት ሲሆን "ሃ" هَا የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም "ሠማኡ አድ-ዱንያ" سَّمَاء الدُّنْيَا ማለትም "ቅርቢቱን ሰማይ" የሚለውን ቃል ተክቶ የመጣ ነው። አሏህ በሌላ አንቀጽ ፀሐይን "ዲያእ" ضِيَاء ጨረቃን ደግሞ "ኑር" نُور ይለዋል፦
ቁርኣን 71፥16 በውስጣቸውም ጨረቃን ኑር አደረገ፥ ፀሐይንም ሲራጅ አደረገ፡፡
وَجَعَلَ الْقَمَرَ فِيهِنَّ نُورًا وَجَعَلَ الشَّمْسَ سِرَاجًا
"ፊ-ሂነ" فِيهِنَّ ማለት "በ-ውስጣቸውም" ማለት ሲሆን "ሂነ" هِنَّ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም "ሰማዋት" سَمَاوَات የሚለውን አንስታይ ብዜት ተክቶ የመጣ ነው፥ ታዲያ ፀሐይ እና ጨረቃ በቅርቢቱ ሰማይ ውስጥ ሆነው ሳሉ ለምን "በሰማያት ውስጥ" ተባሉ? ሲባል ቅርቢቱ ሰማይ ከሰባቱ ሰማያት ውስጥ የመጀመሪያይቱ ሰማይ ናት፦
ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
ስለ ኢሥራእ በዝነኛ ሐዲስ አነሥ”ረ. ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ጂብሪል ከእኔ ጋር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ወጣ፥ እንዲከፈት ተጠየቀ። ዘበኛው፦ “ይህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀ፥ ጂብሪልም፦ “ጂብሪል” አለ። “ከአንተ ጋር ያለውስ? እርሱም፦ “ሙሐመድ ነው” አለ። ከዚያም በተመሳሳይ ወደ ሁለተኛ፣ ወደ ሦስተኛ፣ ወደ አራተኛ እና ወደተቀሩት ሰማያት ሁሉ ወጣ። የሁሉም ሰማይ በር ላይ “ይህ ማን ነው? ተብሎ ተጠየቀ፥ “ጂብሪል ነው” ተባለ”።
عن أنس رضي الله عنه في حديثه المشهور في الإسراء قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : “ثم صعد بي جبريل إلي السماء الدنيا فاستفتح، فقيل: من هذا؟ قال: جبريل، قيل:ومن معك؟ قال: محمد. ثم صعد إلي السماء الثانية والثالثة والرابعة وسائرهن، ويقال في باب كل سماء: من هذا؟ فيقول: جبريل”
ለምሳሌ፦ "እኔ የምኖረው አፍሪካ ውስጥ ነው" ብል "ኢትዮጵያ ውስጥ ነው" ለማለት ፈልጌ እንጂ "ታንዛኒያ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ ወዘተ ውስጥ ነው" ማለት አይደለም፥ በተመሳሳይ "ፀሐይ እና ጨረቃ በሰማያት ውስጥ ናቸው" ሲባል "ከሰባቱ ሰማያት የመጀመሪያይቱ ሰማይ ቅርቢቱ ሰማይ ውስጥ ናቸው" ማለት ነው። በተጨማሪ መላእክት የሚኖሩት በሰባተኛው ሰማይ ላይ እንደሆነ እሙን እና ቅቡል ነው፦
ቁርኣን 40፥7 እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እና እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡
الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 176
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም አሉ፦ "ከእናንተ ውስጥ አንዱ "አሚን" በሚልበት ጊዜ በሰማይ ውስጥ ያሉት መላእክት "አሚን" ይላሉ"።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِذَا قَالَ أَحَدُكُمْ آمِينَ. وَقَالَتِ الْمَلاَئِكَةُ فِي السَّمَاءِ آمِينَ.
ነገር ግን መላእክት በሰባተኛ ሰማይ ቢኖሩም ሰባተኛ ሰማይ የሰማያት ክፍል ስለሆነ መልአክ በሰማያት ውስጥ እንደሚኖር ተገልጿል፦
ቁርኣን 53፥26 "በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም" ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጂ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡
وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ
ፀሐይ እና ጨረቃ በሰማያት ውስጥ መደረግን በዚህ ልክ እና መልክ መረዳት ነው እንጂ "ቁርኣን ስለ ሥነ-አጽናፈ ዓለም ጥናት"cosmology" ያለው ምልከታ የተሳሳተ ነው" ብሎ ያለ ዕውቅት የውሸት ድሪቶ በቅሰጣ ስልቻ ውስጥ መደረት ተገቢ አይደለም፥ እኛም "ከባዶ አንድ ሰርዶ" ብለን ከሚነሱ ቅሰጣዎች አንዱ ለሆነውን ቅሰጣ መልስ ሰተናል። ፀሐይ እና ጨረቃ የአሏህ ተአምራት ናቸው፦
ቁርኣን 41፥37 ሌሊትና ቀንም፥ ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፡፡
وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 16, ሐዲስ 9
አቢ በክራህ" እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም አሉ፦ "ፀሐይ እና ጨረቃ ከአሏህ ተአምራት መካከል ሁለት ተአምራት ናቸው"።
عَنْ أَبِي بَكْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " إِنَّ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ آيَتَانِ مِنْ آيَاتِ اللَّهِ،
"አያህ" آيَة ማለት "ምልክት" "ታምር" ማለት ሲሆን "አያት" آيَتَان ማለት ደግሞ "ምልክቶች" "ታምራት" ማለት ነው፥ በእርግጥም ፀሐይ እና ጨረቃ ከአሏህ ተአምራት መካከል ሁለት ተአምራት ናቸው። አሏህ ቀሳጢዎችን ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛን ጽናቱን ይስጠን! አሚን።
✍ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም