ፈጣሪ ሰውን አይፈትንም ወይስ ይፈትናል?

A. አይፈትንም፦

ያዕቆብ 1፥13 ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ፡ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።

B. ይፈትናል፦

ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው፦ አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፦ እነሆ፥ አለሁ፡ አለ።

አንዳንድ ሰዎች ይህንን ዓይን ያስፈጠጠ እና ጥርስ ያስገጠጠ ግጭት በቋንቋ ሊደበቁ ይሞክራሉ። በቋንቋ ሙግትም እንመልከት፦

ያዕቆብ 1፥13 ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ፡ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።
Μηδεὶς πειραζόμενος λεγέτω ὅτι Ἀπὸ Θεοῦ πειράζομαι· ὁ γὰρ Θεὸς ἀπείραστός ἐστιν κακῶν, πειράζει δὲ αὐτὸς οὐδένα.

እዚህ አንቀጽ ላይ በአፍራሽ ቅጽል ታክሎ የመጣው ግሥ "ፔይራዞኢ" πειράζει ሲሆን ፈጣሪ ማንንም እንደማይፈትን ይናገራል። በተቃራኒው ፈጣሪ አብርሃምን እንደፈተነው ዘፍጥረት ላይ ተዘግቧል፦

ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው፦ አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፦ እነሆ፥ አለሁ፡ አለ።
ΚΑΙ ἐγένετο μετὰ τὰ ρήματα ταῦτα ὁ Θεός ἐπείρασε τὸν ῾Αβραὰμ καὶ εἶπεν αὐτῷ·

እዚህ አንቀጽ ላይ ግሪክ ሰፕቱአጀንትን ላይም "ፈተነው" ለሚለው ግሥ የገባው ቃል በተመሳሳይ "ፔይራዞኢ" ἐπείρασε ነው።

ማንን እንስማ? አይፈትንም የሚለውን ወይስ ይፈትናል የሚለውን?

✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom