በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

” وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ سورت الذاريات”

በራሳችሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ፥ ታዲያ አትመለከቱምን?

ቁርኣን 51፥21

በግዕዝ "ሰብእ" ማለት "ሰው" ማለት ሲሆን ስለ ሰው በመስኩ ምሁራን ዘንድ የሚጠናው ጥናት "ሥነ-ሰብእ ጥናት"anthropology" ይሉታል፥ ይህም ቃል "አንትሮፖስ" ἄνθρωπος ማለትም "ሰው" እና ‎"ሎጊአ" λογία ማለትም "ጥናት" ከሚል ሁለት የግሪክ ቃላት የተዋቀረ ነው። በቁርኣን "ኢንሣን" إِنسَٰن ማለት "ሰው" ማለት ሲሆን ይህም ቃል በነጠላ የተጠቀሰው 65 ጊዜ ብቻ ነው፥ ሰው የተፈጠረው ደግሞ ከአፈር፣ ከፍትወት ጠብታ፣ ከረጋ ደም፣ ከቁራጭ ሥጋ፣ ከአጥንት እና ከጡንጫ ሥጋ ነው፦

”وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن سُلَالَةٍ مِّن طِينٍ ”

በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፡፡

ቁርኣን23፥12

ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ

ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው፡፡

ቁርኣን 23፥13

” مَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

ከዚያም ጠብታዋን የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡

ቁርኣን 23፥14

ሰው የአፈር፣ የፍትወት ጠብታ፣ የረጋ ደም፣ የቁራጭ ሥጋ፣ የአጥንት እና የጡንጫ ሥጋ ሁሉ ድምር ነው፥ ይህንን በዝርዝር ማየት እንችላለን፦

  1. "ቱራብ" تُرَاب ማለት "አፈር" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 17 ጊዜ ብቻ ነው።
  2. "ኑጥፋህ" نُّطْفَة ማለት "የፍትወት ጠብታ" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 12 ጊዜ ብቻ ነው።
  3. "ዐለቃህ" عَلَقَة ማለት "የረጋ ደም" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 6 ጊዜ ብቻ ነው።
  4. "ሙድጋህ" مُضْغَة ማለት "ቁራጭ ሥጋ" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 3 ጊዜ ብቻ ነው።
  5. "ዐዝም" عَظْم ማለት "አጥንት" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 15 ጊዜ ብቻ ነው።
  6. "ለሕም" لَحْم ማለት "የጡንጫ ሥጋ " ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 12 ጊዜ ብቻ ነው።

በድምሩ = 65 ቁጥር ይሆናል።

ይህም "ኢንሣን" إِنسَٰن የሚለው ቃል 65 ጊዜ መጠቀሱ ያለምክንያት አልነበረም፥ አሏህ ነገር ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ስለሆነ ነው፦

” لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا”

እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበ እና "ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን" የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል፡፡

ቁርኣን 72፥28

"ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! በራሳችን ውስጥ ብዙ ተአምራት አሉ፥ ከእኛ የሚጠበቀው መመልከት ብቻ ነው፦

وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ سورت الذاريات

በራሳችሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ፥ ታዲያ አትመለከቱምን?

ቁርኣን51፥21

✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም