በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 47፥4 "እነዚያንም የካዱትን በጦር ላይ ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኃይል ምቱ"፡፡
فَإِذَا لَقِيتُمُ الَّذِينَ كَفَرُوا فَضَرْبَ الرِّقَابِ حَتَّىٰ
ሙሽሪኮች ምእመናንን በበድር ዘመቻ ላይ ሊዋጉ ሲመጡ አምላካችን አሏህ ለምእመናን፦ "እነዚያንም የካዱትን በጦር ላይ ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኃይል ምቱ" አላቸው፦
ቁርኣን 47፥4 "እነዚያንም የካዱትን በጦር ላይ ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኃይል ምቱ"፡፡ فَإِذَا لَقِيتُمُ الَّذِينَ كَفَرُوا فَضَرْبَ الرِّقَابِ حَتَّىٰ
በዚህ በድር ዘመቻ ላይ አሏህ መላእክትን ልኳል፥ ለምእመናን ሦስት ሺህ መላእክትን ለዘመቻው እንዲረዱ አድርጓል። ቢታገሱ እና ቢጠነቀቁ ደግሞ በአምስት ሺህ መላእክት እንደሚረዳ ተናግሯል፥ ሦስት ሺህ እና አምስት ሺህ ተከታታዮች ሲኾኑ እረድቷቸዋል፦
ቁርኣን 3፥123 በበድርም እናንተ ጥቂቶች ኾናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ፡፡ አላህንም ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት፡፡
وَلَقَدْ نَصَرَكُمُ اللَّهُ بِبَدْرٍ وَأَنتُمْ أَذِلَّةٌ ۖ فَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
ቁርኣን 3፥124 ለምእምናን «ጌታችሁ በሦስት ሺህ መላእክት የተወረዱ ሲኾኑ ቢረዳችሁ አይበቃችሁምን?» በምትል ጊዜ አስታውስ፡፡
إِذْ تَقُولُ لِلْمُؤْمِنِينَ أَلَن يَكْفِيَكُمْ أَن يُمِدَّكُمْ رَبُّكُم بِثَلَاثَةِ آلَافٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُنزَلِينَ
ቁርኣን 3፥125 «አዎን ብትታገሱ እና ብትጠነቀቁ ከዚህም ፍጥነታቸው ጠላቶቻችሁ ቢመጡባችሁ ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላእክት ይረዳችኋል፡፡»
بَلَىٰ ۚ إِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا وَيَأْتُوكُم مِّن فَوْرِهِمْ هَـٰذَا يُمْدِدْكُمْ رَبُّكُم بِخَمْسَةِ آلَافٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُسَوِّمِينَ
ቁርኣን 8፥9 ከጌታችሁ ርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲኾኑ እረዳችኋለሁ» ሲል ለናንተ የተቀበላችሁን አስታውሱ፡፡
إِذْ تَسْتَغِيثُونَ رَبَّكُمْ فَاسْتَجَابَ لَكُمْ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلْفٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُرْدِفِينَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ሺህ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አልፍ" أَلْف ሲሆን ሙጅመል ነው፥ በሙፈሰል ደግሞ "ሦስት" እና "አምስት" በሚለው የገባው ቃል "ኣላፍ" آلَاف ሲሆን መላእክቱ "ተከታታዮች" ሲሆኑ የሚለው በሦስት ሺህ እና በአምስት ሺህ ቁጥር መምጣታቸውን ያሳያል። በበድር ዘመቻ አምላካችን አሏህ ለእነዚህ መላእክት፦ "እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ! በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፡፡ ከአንገቶችም በላይ ምቱ! ከእነርሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ" በማለት አዘዛቸው፦
ቁርኣን 8፥12 ጌታህ ወደ መላእክቱ «እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ! በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፡፡ ከአንገቶችም በላይ ምቱ! ከእነርሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ!» ሲል ያወረደውን አስታውስ፡፡ إِذْ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى الْمَلَائِكَةِ أَنِّي مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا الَّذِينَ آمَنُوا ۚ سَأُلْقِي فِي قُلُوبِ الَّذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ فَاضْرِبُوا فَوْقَ الْأَعْنَاقِ وَاضْرِبُوا مِنْهُمْ كُلَّ بَنَانٍ
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚሽነሪዎች ወቃሽና ነቃሽ ሆነው፦ "መላእክት እንዴት የሰው አንገት ይቀላሉ" በማለት ባዕዳና እንግዳ ያልሆነ እና ያረጀና ያፈጀ ጥያቄ ይጠይቃሉ፥ እኛም ስልመልስ ባይብል ስለ ሰይፍ የሚናገረውን ጠንቅቆ ካለማንበብ የሚመጣ ጥያቄ ነው በማለት እንመልሳለን። በባይብል የእግዚአብሔር መላእክት የተመዘዘ ሰይፍ በእጃቸው እንደሚይዙ ብዙ ቦታ ይናገራል፦
ዘኍልቍ 22፥23 አህያይቱም የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤
ዘኍልቍ 22፥31 የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።
ኢያሱ 5፥13 የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር"*።
1ኛ ዜና 21፥16 "ዳዊትም ዓይኖቹን አነሣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ"።
ይህ ሰይፍ አንባሻ ቆርሰው የሚያበሉበት ሳይሆን የሰው አንገት የሚቀሉበት ነው፥ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔርም መልአክ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደሎ ነበር፦
ኢሳይያስ 37፥36 "የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ"።
ድርሳነ ዑራኤል ላይ መልአኩ ዑራኤል ሰይፍ ይዞ አንድ ሰውን፦ "ከሁለት ቦታ እቆርጥሃለው" ሲለው ይደመጣል፦
ድርሳነ ዑራኤል ዘሚያዚያ ገፅ 174 ቁጥር 11 "ቅዱስ ዑራኤል በሚያስፈራ ግርማ የተሳለ ሰይፉን ይዞ፦ "አንተ የነገርኩህን ነገር ለምን አቦዘንከው? አሁንስ ከሁለት ቦታ እቆርጥሃለው" አለው"።
በተመሳሳይ ወደ ሰዎች ስንመጣ የያዕቆብ ልጆች ስምዖን እና ሌዊ እኅታቸው ዲና በመደፈሯ ሰይፋቸውን ይዘው ወንዱንም ሁሉ ገደለው እና ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ፦
ዘፍጥረት 34፥25-26 "የዲና ወንድሞች የያዕቆብ ልጆች ስምዖን እና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ሳይፈሩ ወደ ከተማ ገቡ፥ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ። ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ"።
ፈጣሪ ለያዕቆብ ልጆች፦ "የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፣ ከተማይቱን በእርስዋም ያለውን ሁሉ፣ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፋቸዋለህ" ብሏቸዋል፥ እነርሱም በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፣ ወንዱንና ሴቱን፣ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፣ በሬውንም በጉንም አህያውንም በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ፦
ዘዳግም 13፥15 "የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፤ ከተማይቱን፥ በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፋቸዋለህ"።
ኢያሱ 6፥21 በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።
ይህንን የሰይፍ መጽሐፍ ስናብራራ ሚሽነሪዎች፦ "ይህ እኮ በብሉይ ኪዳን እንጂ በአዲስ ኪዳን ስለ ሰይፍ አያወራም" በማለት ባይብሉን ቀጋና አልጋ ለማድረግ ይፈልጋሉ፥ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ፦ "ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ" ብሎ አዘዘዘ፦
ሉቃስ 22፥36 "እርሱም፦ አሁን ግን ኮረጆ ያለው ከእርሱ ጋር ይውሰድ፥ ከረጢትም ያለው እንዲሁ፤ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ"።
ይህ ለመከላከል የተደረገ የጦር ስልት ሲሆን ከሐዋርያቱ አንዱ በመቸኮል ወደ ማጥቃት ገብቶ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘ እና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው፦
ማቴዎስ 26፥51 "እነሆም ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘ እና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው"።
በሙሴ ሸሪዓህ የገደለ ይገደል የሚል ነውና ኢየሱስም፦ "ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ" አለው፦
ማቴዎስ 26፥52 ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ።
"ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ" ማለት ሰይፍን አንስቶ በሰይፍ ያለ አግባብ የሚገድል እራሱ በሰይፍ ይገደላል ማለት ነው፦
ራእይ 13፥10 "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል"።
ልብ አድርግ ራእይ 1፥1-2 ላይ ራእዩ ከእግዚአብሔር ለኢየሱስ ከኢየሱስ ለመልአኩ ከመልአኩ ወደ ዮሐንስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ይናገራል፥ ይህ "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል" የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ላይ ያለ ቃል ነው። ማንበብ ሙሉ ሰው ያረጋልና አንብቡ! አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።
✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም