በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ቁርኣን 16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡
إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ግብጻዊ ቄስ ዘካሪያስ لَعْنَتَ اللَّهِ عَلَيْهِ ሁልጊዜ ለሚቀጥፈው ቅጥፈት ምላሽ ሲሰጠው እየተገለባበጠ ኢሥላምን የሚያጠለሽበት ጥላሸት ለመፈለግ ቀን ከሌሊት ይዳክራል፥ ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው። እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፦

ቁርኣን 16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡
إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ከቀጠፈው ቅጥፈት አንዱ ነቢያችንን”ﷺ” ከሬሳ ጋር ተራክቦ እንዳደረጉ አድርጎ መቅጠፉ ነው፥ ወሊ-አዑዝቢሏህ እኔ ለደገሙት ቃል ሰቀጠጠኝ። ኅሊናውን ለሸጠ ሰው እና ሐሰትን ለተከናነበ ሰው ይህን ማድረግ ውስጡን ሰላም አይሰጠውም። እስቲ የሚያነሳቸውን ሐዲሳት እንመልከት፦

ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 23, ሐዲስ 98
አነሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ”የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ሴት ልጅ የቀብር ሥርአት ላይ ነበርን፤ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” በመቃብር አቅራቢያ ተቀምጠው ዓይኖቻቸው በእንባ ሞልተው አየዋቸው፤ እርሳቸውም፦ “ከመካከላችሁ በዚህ ሌሊት ከሚስቱ ጋር ተራክቦ ያላደረገ አለን? አሉ፤ አቡ ጠልሓህም፦ “እኔ አለሁ” ብሎ መለሰ፤ እርሳቸውም፦ “ወደ መቃብሯ ውረድ” አሉት፤ እርሱም ወደ መቃብሯ ወረዶ ቀበራት"።
عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ شَهِدْنَا بِنْتَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَرَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم جَالِسٌ عَلَى الْقَبْرِ، فَرَأَيْتُ عَيْنَيْهِ تَدْمَعَانِ فَقَالَ ‏”‏ هَلْ فِيكُمْ مِنْ أَحَدٍ لَمْ يُقَارِفِ اللَّيْلَةَ ‏”‌‏.‏ فَقَالَ أَبُو طَلْحَةَ أَنَا‏.‏ قَالَ ‏”‏ فَانْزِلْ فِي قَبْرِهَا ‏”‌‏.‏ فَنَزَلَ فِي قَبْرِهَا فَقَبَرَهَا‏.‏

ከመነሻው እዚህ ሐዲስ ላይ፦ "እከሌ ከሬሳ ጋር ወሲብ ፈጸመ" የሚል ሽታው እንኳን ቢፈለግ የለም፥ ውሸት ሲጋለጥ ከዚህ ይጀመራል።
ሲቀጥል “ኔክሮፊሊያ”Necrophilia” ማለት ከሬሳ ጋር የሚደረግ ተራክቦ ነው፥ በኢሥላም አይደለም ከሞተ ሰው ይቅርና በቁም ካለ ሰው ጋር ተራክቦ ለማድረግ ኒካሕ ይወጅባል። እስቲ ሁለተኛውን ሐዲስ እንመልከት፦
ከንዙል ዑማል 242218
ኢብኑ አባስ እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ”የጀነትን ልብስ እስከምትለብስ ልብሴን አለበስኳት፣ በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ፣ ምናልባት የመቃብሩ ጫና ይቀንሳል ብዬ። ለእኔ ከአቡ ጠሊብ በኃላ ከአላህ ፍጥረት በላጭ ናት። ነቢዩም”ﷺ” ይህንን ያሉት የዐሊይ እናት ስለሆነችው ስለፋጢማ ነበር"።

“ከንዙል ዑማል” كنز العمال ማለት “የሠናይ ገባሪ ጥሪኝ” ማለት ነው፥ ዐሊ ኢብኑ ዐብዱል ማሊክ አል-ሂንዲ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1517 ድህረ-ልደት ያዘጋጀው ሐዲስ ነው።
፨ሲጀመር ይህ ሐዲስ ከመነሻው ዶዒፍ ነው።
፨ሲቀጥል የዐሊይ እናት ለነቢያችን”ﷺ” አክስት ናት፥ ከአቡ ጠሊብ ጋር ሆና ያሳደገቻቸው እርሷ ናት። ከአክስት ጋር አይደለም ሞታ ወሲብ ይቅርና በቁምም ከአክስት ጋር ጋብቻ ክልክል ነው፦

ቁርኣን 4፥23 እናቶቻችሁ፣ ሴት ልጆቻችሁም፣ እኅቶቻችሁም፣ "አክስቶቻችሁም፣ የሹሜዎቻችሁም፣" የወንድም ሴቶች ልጆችም፣ የእኅት ሴቶች ልጆችም፣ እነዚያም ያጠቡዋችሁ እናቶቻችሁ፣ ከመጥባት የኾኑትም እኅቶቻችሁ፣ የሚስቶቻችሁም እናቶች፣ እነዚያም በጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ በእነርሱ የገባችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴቶች ልጆች፣ "ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ"፡፡
حُرِّمَتْ عَلَيْكُمْ أُمَّهَاتُكُمْ وَبَنَاتُكُمْ وَأَخَوَاتُكُمْ وَعَمَّاتُكُمْ وَخَالَاتُكُمْ وَبَنَاتُ الْأَخِ وَبَنَاتُ الْأُخْتِ وَأُمَّهَاتُكُمُ اللَّاتِي أَرْضَعْنَكُمْ وَأَخَوَاتُكُم مِّنَ الرَّضَاعَةِ وَأُمَّهَاتُ نِسَائِكُمْ وَرَبَائِبُكُمُ اللَّاتِي فِي حُجُورِكُم مِّن نِّسَائِكُمُ اللَّاتِي دَخَلْتُم بِهِنَّ فَإِن لَّمْ تَكُونُوا دَخَلْتُم بِهِنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ وَحَلَائِلُ أَبْنَائِكُمُ الَّذِينَ مِنْ أَصْلَابِكُمْ وَأَن تَجْمَعُوا بَيْنَ الْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

፨ሢሰልስ “በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ” اضْطَجَعَ معها في قبرها ማለት “ወሰብኩኝ” “ተራከብኩኝ” ብሎ የተረጎመላችሁ ማን ነው? “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ ማለት “ተኛ” ማለት እንጂ “ወሰበ” አሊያም “ተራከበ” ማለት አይደለም። ይህ ዐረቢኛው ባይብል ላይ ኤልሳዕ ከሕፃኑ ጋር የተኛውን ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል፦

2 ነገሥት 4፥34 መጥቶም በሕፃኑ ላይ "ተኛ"፤ አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ "ተጋደመበት"፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ።
ثُمَّ صَعِدَ وَاضْطَجَعَ فَوْقَ الصَّبِيِّ وَوَضَعَ فَمَهُ عَلَى فَمِهِ وَعَيْنَيْهِ عَلَى عَيْنَيْهِ وَيَدَيْهِ عَلَى يَدَيْهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተኛ” ለሚለው ቃል የገባው ቃል “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ታዲያ ኤልያስ ከሕጻኑ ጋር ወሲብ አደረገ ማለት ነውን? አዎ ካላችሁን ነብዩ ኤልሳዕ ግብረ ሰዶማዊ ነው ልትሉ ነው? ምክንያቱም ሕጻኑ ወንድ ሕጻን ነውና። አይ “ተወሰበ” “ተራከበ” ለሚለው ቃል “ነከሐ” نَكَحَ እንጂ “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈታችሁን እዚህ ጋር ይብቃ! ምነው በተመሳሳይ ሙሴ ከአባቶቹ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ ፈጣሪ ነግሮታል፥ በተጨማሪም ኢዮብ ሰው ከአጥንቱ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ ተናግሯል። ኢሳይያስም ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል ብሏል፦

ዘዳግም 31፥16 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ትተኛለህ
وَقَال الرَّبُّ لِمُوسَى: «هَا أَنْتَ تَرْقُدُ مَعَ آبَائِك
ኢዮብ 20፥11 አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ "ይተኛል"።
عِظَامُهُ مَلآنَةٌ قُوَّةً وَمَعَهُ فِي التُّرَابِ تَضْطَجِعُ.
ኢሳይያስ 11፥6 ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር "ይተኛል"፤
فَيَسْكُنُ الذِّئْبُ مَعَ الْخَرُوفِ وَيَرْبُضُ النَّمِرُ مَعَ الْجَدْيِ وَالْعِجْلُ

ሰው በመሬት ውስጥ “ይተኛል” ለሚለው ቃል የወደፊት ግስ የተጠቀመበት “ተድጦጂዑ” تَضْطَجِعُ ሲሆን የእርሱ አላፊ ግስ “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ ነው፥ እና ሰው አፈር ውስጥ ወሲብ ያረጋል ማለቱ ነውን? እረ “መተኛት” ሲባል "ተራክቦ ወይም ወሲብ ማለት አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈት ይብቃ! ከላይ ያለውን ዶዒፍ ሐዲስ በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም