በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ቁርኣን 22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ፡፡
فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ ትክክለኛ ንግግር መናገር ነው፥ አንድ አማኝ ትክክለኛውንም ንግግር መናገር እና የሐሰትን ቃል መራቅ አለበት፦

ቁርኣን 33፥70 እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ።
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا
ቁርኣን 22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ፡፡
فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

“ባጢል” ْبَاطِل ማለት “ሐሰት” “ውሸት” “ቅጥፈት” ማለት ነው። እውነተኛ ሰው በማስረጃ እና በዕውቀት ይናገራል፥ ከእውነተኞችም ጎን ይቆማል፦

ቁርኣን 2፥111 እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ በላቸው፡፡

قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
ቁርኣን 6፥143 "እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ" በላቸው፡፡
نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
ቁርኣን 9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

ሰሞኑን ዶዒፍ ሐዲስ ሳይሆን ለሚድያ ማሞቂያ ረሡል"ﷺ" ያላሉትን እንዳሉ እየተደረገ እየተቀጠፈ ይገኛል፥ ምንጭ አልባ እና ሰነድ አልባ ሐዲስ ሲነገራችሁ ፈትሹት! ማንም ሆን ብሎ በተወዳጁ ነቢይ "ﷺ" ላይ የሚቀጥፍ መቀመጫው እሳት ነው፦

ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 41, ሐዲስ 15
ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ሆን ብሎ በእኔ ላይ የሚቀጥፍ መቀመጫው እሳት ነው"።
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ كَذَبَ عَلَىَّ مُتَعَمِّدًا فَلْيَتَبَوَّأْ مَقْعَدَهُ مِنَ النَّارِ ‏"‏ ‏.‏

አሏህ ፈሣድ ከሚያስፋፉ ሙፍሢዲን ይጠብቀን! አሚን።

✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም