በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 75፥2 ራሷን ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡
وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ
"ነፍሥ" نَّفْس የሚለው ቃል "እራስ"own self" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ "ቀተለ ነፍሠ-ሁ" قَتَلَ نَفْسَهُ ስንል "እራሱን አጠፋ" ማለት ነው፣ "ረአይቱ ነፍሢ ፊል መርኣህ" رَأَيْتُ نَفْسِي فِي ٱلْمِرْآةِ ስንል "እራሴን በመስታዎት አየሁኝ" ማለት ነው። "ዶሚሩ አን-ነፍሢያህ" ضَمِير الْنَفْسِيَّة ማለት እራሱ "ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun” ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" አምላካችን አሏህ ያዘዛቸው ላይ "እራሴ" ሲሉ "ነፍሢ” نَفْسِي በማለት እንዲሉ ተናግሯል፦
ቁርኣን 7፥188 በላቸው፦ "አላህ የሻውን በስተቀር "ለ-"እራሴ" ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም፡፡
قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ
በዚህ አንቀጽ ላይ "እራሴ"my-self" ለሚለው የገባው ቃል "ነፍሢ" نَفْسِي መሆኑ ልብ አድርግ! ይህ ያቀረብነው ናሙና በመጀመርያ መደብ ሲሆን አሏህ በሁለተኛ መደብ "እራስህ" ለማለት "ነፍሢከ" نَفْسِكَ በማለት ይናገራል፦
ቁርኣን 4፥79 ከደግም የሚያገኝህ ከአላህ ነው፤ ከፉዉም የሚደርስብህ "ከ-"እራስህ" ነው።
مَّا أَصَابَكَ مِنْ حَسَنَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ۖ وَمَا أَصَابَكَ مِن سَيِّئَةٍ فَمِن نَّفْسِكَ ۚ وَأَرْسَلْنَاكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا
በዚህ አንቀጽ ላይ "ራስህ"your-self" ለሚለው የገባው ቃል "ነፍሢከ" نَفْسِكَ ነው። አሏህ በሦስተኛ መደብ "እራሱ"him-self" ለማለት "ነፍሢሂ" نَفْسِهِ በማለት ይናገራል፦
ቁርኣን 2፥207 ከሰዎችም ውስጥ የአላህን ውዴታ ለመፈለግ "እራሱን" የሚሸጥ ሰው አለ፡፡ አላህም ለባሮቹ በጣም ርኅሩህ ነው፡፡
وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْرِي نَفْسَهُ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ
ስለዚህ በጥቅሉ "ነፍሥ" نَّفْس ማለት "ሁለንተናዊ ማንነት"wholly identity" ማለት ነው፥ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሲገድል "ነፍሰ ገዳይ" ይባላል፦
ቁርኣን 17፥33 ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፡፡
وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ላ ተቅተሉ አን-ነፍሥ" لَا تَقْتُلُوا النَّفْس ማለት "ነፍስን አትግደሉ" ማለት ነው፥ በዚህ ዐውድ "ነፍሥ" نَّفْس የሚለው "አካል" የሚለውን ለማመልከት የገባ ነው፦
ቁርኣን 39፥6 ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፡፡ ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን አደረገ፡፡
خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا
እዚህ አንቀጽ ላይ "አንዲት ነፍሥ" የተባለው አደም ሲሆን "መቀናጆዋን" የተባለችው ከአደም የተፈጠረችው ሐዋን ነው፥ እኛ ሆንን እናታችን ሐዋ ከአደም የተፈጠረው አካላችን ነው። ሩሓችን ግን ከአፈር ሳይሆን ከአሏህ ነው፦
ቁርኣን 17፥85 ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡
وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا
ቁርኣን 39፥62 አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡
اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
"ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው" የሚለው ኃይለ-ቃል በራሱ ሩሕ "ነገር" ውስጥ ስለሚካተት እና አሏህ የሁሉ “ነገር” ፈጣሪ ስለሆነ የማንም ሰው ሩሕ ፍጡር ነው። "ነፍሥ" نَّفْس የሚለው "ሩሕ" رُّوح በሚል ዐውድ ለማመልከት መጥቷል፦
ቁርኣን39፥42 አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፡፡
ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا
"አንፉሥ" أَنفُس የነፍሥ ብዙ ቁጥር ሲሆን በሞት ጊዜ የሚሄደውን መንፈሳችንን ለማልከት የገባ ነው፥ "ሩሕ" رُّوح ማለት “መንፈስ” ማለት ሲሆን "ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል" ማለት አሏህ ሩሓችንን በእንቅልፍ ጊዜ ወስዶ በንቃት ጊዜ ይመልሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 97
አቡ ቀታዳህ እንደተረከው፦ "ከሶላት ሰዎች በተኙ ጊዜ የአሏህ ነቢይም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ በሚሻው ጊዜ ሩሓችሁን ይወስዳል፥ በሚሻው ጊዜ ይመልሳል"።
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي قَتَادَةَ، عَنْ أَبِيهِ، حِينَ نَامُوا عَنِ الصَّلاَةِ، قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم " إِنَّ اللَّهَ قَبَضَ أَرْوَاحَكُمْ حِينَ شَاءَ، وَرَدَّهَا حِينَ شَاءَ "
"አርዋሕ" أَرْوَاح ማለት "መንፈሶች" ማለት ሲሆን "ሩሕ" رُّوح ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አሏህ ነፍሥን በእንቅልፏ ጊዜ ሲወስዳት ያለ ዓይን ታያለች፣ ያለ ጆሮ ትሰማለች፣ ያለ እግር ትሄዳለች፣ ያለ አፍ ትናገራለች።
ስለዚህ በኢሥላም አስተምህሮት ከወላጆች የሚወሰደው አካል እንጂ መንፈስ ስላልሆነ "ከወላጆች ነፍስ ይወሰዳል" ከተባለ አካልን ታሳቢ ባደረገ እንጂ መንፈስን ዋቢ ባደረገ መልኩ ከወላጆች ነፍስ አይወሰድም፥ "አካልን ከወላጆቻችን አካል እንደተገኘ ሁሉ መንፈሳችን ከወላጆቻችን መንፈስ የተገኘ"traduction" ነው" የሚል ተስተምህሮት ዲኑል ኢሥላም ውስጥ የለም። በጥቅሉ ነፍሥ "እራስነት"own self-hood" ነው፦
ቁርኣን 75፥2 ራሷን ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡
وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ
ቁርኣን 89፥27 ለአመነች ነፍስም፦ «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ!
يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ
ቁርኣን 89፥28 ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡
ارْجِعِي إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً
ቁርኣን 89፥29 በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡
فَادْخُلِي فِي عِبَادِي
ቁርኣን 89፥30 ገነቴንም ግቢ» ትባላለች፡፡
وَادْخُلِي جَنَّتِي
አምላካችን አሏህ ያመነችን ነፍስ "ገነቴንም ግቢ" ሲላት አጠቃላይ አካላዊ እና መንፈሳዊ ማንነት ያላትን ነው። አሏህ "ገነቴንም ግቢ" ከሚላት ነፍስ ያድርገን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም