በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 21፥85 ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን አስታውስ! ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው፡፡
وَإِسْمَاعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّابِرِينَ
"ዙ አን-ኑን" ذَا النُّونِ ማለት "የዓሣው ባለቤት" ማለት ሲሆን "ዙል-ቀርነይን" ذِي الْقَرْنَيْن ማለት "የሁለቱ ቀንዶች ባለቤት" ወይም "የሁለቱ ክፍለ-ዘመናት ባለቤት" ማለት ነው፦
ቁርኣን 21፥87 የዓሣውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ አስታውስ፡፡
وَذَا النُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَاضِبًا
ቁርኣን 18፥83 “ስለ ዙል-ቀርነይንም ይጠይቁካል፡፡ «በእናንተ ላይ ከእርሱ ወሬን አነባለሁ» በላቸው”፡፡
وَيَسْأَلُونَكَ عَن ذِي الْقَرْنَيْنِ ۖ قُلْ سَأَتْلُو عَلَيْكُم مِّنْهُ ذِكْرًا
"ዙ" ذَا ማለት በአገዛዛቢ መደብ የመጣ ሲሆን "ባለቤት" ማለት ነው፥ "ኪፍል" كِفْل ማለት "ክፍል" ማለት ሲሆን "ዙልኪፍል" ذَا الْكِفْل ማለት "የክፍል ባለቤት" ማለት ነው። ይህ ነቢይ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ዒራቅ ውስጥ ነበረ፥ እዛ የተወሰነ ክፍል ተሰቶት ይኖር ነበር። ያ የኖረበት ቦታ "ኪፍል" كِفْل ሲባል ነቢዩ ደግሞ "የክፍል ባለቤት" ተብሏል፥ ይህ ነቢይ በቁርኣን ውስጥ ልክ እንደ ኢድሪሥ በማዕረግ ስም ተጠርቷል። የተጸውዖ ስሙ "ሒዝቂያል" حِزْقِيَال ይባላል፥ አይሁዳውያን ኪፍል በሚባል ቦታ የሕዝቅኤልን መቃብር ይጎበኙ ነበር። አምላካችን አሏህ ዙልኪፍልን ከኢስማዒል እና ከኢድሪስ ጋር ያወሳዋል፦
ቁርኣን 21፥85 ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን አስታውስ! ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው፡፡
وَإِسْمَاعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّابِرِينَ
ቁርኣን 21፥86 ከችሮታችንም ውስጥ አገባናቸው፡፡ እነርሱ ከመልካሞቹ ናቸውና፡፡
وَأَدْخَلْنَاهُمْ فِي رَحْمَتِنَا ۖ إِنَّهُم مِّنَ الصَّالِحِينَ
አሏህ ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን ከችሮታው ውስጥ አገባቸው፥ ይህም ችሮታ ወሕይ በማውረድ የሚሰጥ ነቢይነት ነው፦
ቁርኣን 3፥74 በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡
يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ
ቁርኣን 2፥90 አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው (ራእይን) ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው፡፡
أَن يَكْفُرُوا بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ بَغْيًا أَن يُنَزِّلَ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ
አሏህ "ባሪያችንን አዩብን፣ ባሮቻችንን ኢብራሂምን፣ ኢሥሐቅን፣ የዕቁብን አውሳ" ካለ በኃላ "ኢስማዒልን፣ አልየሰዕን፣ ዙልኪፍልን አውሳ! በማለት ከነቢያት ምድብ ውስጥ ይከታቸዋል፥ ኢስማዒል፣ አልየሰዕ፣ ዙልኪፍል ከበላጮቹ ናቸው። አሏህ መጽሐፍን፣ ጥበብን እና ነቢይነትን ሰቷቸዋል፦
ቁርኣን 38፥48 ኢስማዒልን፣ አልየሰዕን፣ ዙልኪፍልን አውሳ! ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው፡፡
وَاذْكُرْ إِسْمَاعِيلَ وَالْيَسَعَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ وَكُلٌّ مِّنَ الْأَخْيَارِ
ቁርኣን 6፥89 እነዚህ እነዚያ መጽሐፍን፣ ጥበብን እና ነቢይነትን የሰጠናቸው ናቸው፡፡
أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ
አምላካችን አሏህ በትንሳኤ ቀን በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት ጋር ያማረ ጓደኛ ያድርገን! አሚን።
✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም