በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥93 ተውራት ከመወረድዋ በፊት ኢሥራኢል በራሱ ላይ እርም ካደረገው ነገር በስተቀር ምግብ ሁሉ ለኢሥራኢል ልጆች የተፈቀደ ነበር፡፡ كُلُّ الطَّعَامِ كَانَ حِلًّا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ إِلَّا مَا حَرَّمَ إِسْرَائِيلُ عَلَىٰ نَفْسِهِ مِن قَبْلِ أَن تُنَزَّلَ التَّوْرَاةُ

"ኢላህ" إِلٰه ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን "ኢል" ئِيل ደግሞ "ኢላህ" إِلٰه ለሚለው ምጻረ ቃል"Abbreviation" ነው፥ "ኢሥራእ" إِسْرَاء የሚለው ቃል "አሥራ" أَسْرَى ማለትም "አስጓዘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ጉዞ" ማለት ነው፦

17፥1 ያ ባሪያውን ከተከበረው መሥጂድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መሥጂድ በሌሊት ውስጥ ያስጓዘው ጥራት ይገባው! ከተአምራታችን ልናሳየው አስጓዝነው፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا

"ያስጓዘ" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "አሥራ" أَسْرَىٰ ሲሆን "ሡረቱል ኢሥራእ" سُورَة إِسْرَاء እራሱ "ሡረቱል በኒ ኢሥራኢል" سُورَة بَنِي إِسْرَائِيل ይባላል፥ ኢማም ቡኻርይ

መጽሐፍ 66, ሐዲስ 16 ተመልከት!
"ኢሥራኢል" إِسْرَائِيل ማለት "አምላክ አስጓዘ" ማለት ነው። "አሥራ" أَسْرَاء ማለት "በታች መገዛት" ማለት ሲሆን ደግሞ "ኢሥራኢል" إِسْرَائِيل ማለት "የአምላክ ባሪያ" ማለትም ነው፦
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 2፥40 "ዐብደሏህ ኢብኑ ዐባሥ እንደተናገረው፦ "ኢሥራኢል" ማለት "የአሏህ ባሪያ" ማለት ነው"። عن عبد الله بن عباس أن إسرائيل كقولك : عبد الله

"ሣረ" سَارَ ማለት "ገዛ" ማለት ሲሆን ለምሳሌ፦ የኢብራሂም ሚስት "ሣራህ" سَارَة ማለት "ልዕልት" "ንግሥት" ማለት ነው፥ በዚህ አግባብ "ኢሥራኢል" إِسْرَائِيل ማለት "አምላክ ይገዛል" ማለትም ነው።
እዚህ ድረስ ስለ ስሙ አመጣጥ ከተግባባን ዘንዳ ታዲያ ኢሥራኢል ማን ነው? ኢሥራኢል ከተውራት በፊት የነበረ አንድ ግለሰብ"Individual" ሲሆን እርሱም የዕቁብ ነው፦

3፥93 ተውራት ከመወረድዋ በፊት ኢሥራኢል በራሱ ላይ እርም ካደረገው ነገር በስተቀር ምግብ ሁሉ ለኢሥራኢል ልጆች የተፈቀደ ነበር፡፡ كُلُّ الطَّعَامِ كَانَ حِلًّا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ إِلَّا مَا حَرَّمَ إِسْرَائِيلُ عَلَىٰ نَفْسِهِ مِن قَبْلِ أَن تُنَزَّلَ التَّوْرَاةُ

ይህ ኢሥራኢል ብዙ ልጆች ስላሉት ልጆቹ "የኢሥራኢል ልጆች" ተብለዋል፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" እንቅጩን ፍርጥ አርገው ኢሥራኢል "የዕቁብ" يَعْقُوب እንደሆነ ነግረውናል፦

2፥40 የኢሥራኢል ልጆች ሆይ! ያችን በእናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬን አስታውሱ፡፡ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اذْكُرُوا نِعْمَتِيَ الَّتِي أَنْعَمْتُ عَلَيْكُمْ
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 2፥40 "ዐብደሏህ ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ከየሁዲ ጭፍሮች ወደ ነቢዩ"ﷺ" መጥተው እርሳቸውም ለእነርሱ፦ "ኢሥራኢል የዕቁብ እንደሆነ ታውቃላችሁን? አሏቸው፥ እነርሱም፦ "በአሏህ ይሁንብን አዎ" አሉ። ነቢዩ"ﷺ"፦ "አሏህ ሆይ! ምስክር ሁን" አሉ"። حدثني عبد الله بن عباس قال : حضرت عصابة من اليهود نبي الله صلى الله عليه وسلم ، فقال لهم : هل تعلمون أن إسرائيل يعقوب ؟ . قالوا : اللهم نعم . فقال النبي صلى الله عليه وسلم : اللهم اشهد

የሐዲሱ ደረጃ ሶሒሕ ነው፥ ኢማም አሕመድ ቁጥር 2514 ላይ ይህ ሐዲስ ተዘግቧል። ምን ትፈልጋለህ? ቁርኣናዊ ማስረጃስ ይኖር ይሆን? አሏህ ሡረቱል በቀራህ 2፥40 ላይ "የኢሥራኢል ልጆች ሆይ" ካለ በኃላ ዐውደ ንባቡን ስንከተል በሁለተኛ መደብ "በእናንተ ላይ ደመናን አጠለልን፥ በእናንተ ላይ መናን እና ድርጭትን አወረድን" በማለት ይናገራል፦

2፥57 በእናንተ ላይ ደመናን አጠለልን፥ በእናንተ ላይ መናን እና ድርጭትን አወረድን፡፡ وَظَلَّلْنَا عَلَيْكُمُ الْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْكُمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ
በሌላ ጥቅስ ላይ በሦስተኛ መደብ "በእነርሱ ላይ ደመናን አጠለልን፥ በእነርሱ ላይ መናንና ድርጭትን አወረድን" በማለት ይናገራል፦
7፥160 በእነርሱ ላይ ደመናን አጠለልን፥ በእነርሱ ላይ መናንና ድርጭትን አወረድን፡፡ وَظَلَّلْنَا عَلَيْهِمُ الْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْهِمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ

እዚሁ አንቀጽ ላይ የኢሥራኢል ልጆችን አሥራ ሁለት ነገዶች አርጎ እንደከፋፈላቸው ይናገራል፦

7፥160 አሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው፡፡ وَقَطَّعْنَاهُمُ اثْنَتَيْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا

"ሠበጥ" سَبَط ማለት "ነገድ" ማለት ነው፥ "አሥባጥ" أَسْبَاط ደግሞ "ሠበጥ" سَبَط ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን "ነገዶች" ማለት ነው። አሥራ ሁለት ነገዶች አሥራ ሁለቱ የየዕቁብ ልጆች ናቸው፦

4፥163 እኛ ወደ ኑሕ እና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፥ ወደ ኢብራሂም፣ ወደ ኢስማዒል፣ ወደ ኢሥሓቅ፣ ወደ የዕቁብ፣ ወደ "ነገዶቹም"፣ ወደ ዒሣ፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑሥ፣ ወደ ሃሩን፣ ወደ ሱለይማን አወረድን፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ


"ወደ የዕቁብ" ካለ በኃላ "ወደ ነገዶቹም" ማለቱ በራሱ አሥራ ሁለት ነገዶች የኢሥራኢል ልጆች እንደሆኑ በቂ ማሳያ ነው፥ እዚሁ አንቀጽ ላይ "ነገዶቹ" ለሚለው የገባው ቃል በተመሳሳይ "አሥባጥ" أَسْبَاط ነው። አሏህ ወደ አሥራ ሁለቱ ነገዶች ወሕይ አውርዷል፥ ከእነርሱ ጋር ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ይዟል፦

5፥12 አሏህ የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው፡፡ ከእነርሱም አሥራ ሁለትን አለቆች አስነሳን፡፡ وَلَقَدْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَبَعَثْنَا مِنْهُمُ اثْنَيْ عَشَرَ نَقِيبًا

የእስራኤልን ልጆች አሥራ ሁለቱ አለቆች መሆናቸውን ከተግባባን አሥራ ሁለቱ የእስራኤልን ልጆች የየዕቁብ ልጆች ናቸው፦

12፥4 ዩሱፍ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ አሥራ አንድ ከዋክብትን፣ ፀሐይን እና ጨረቃን በሕልሜ አየሁ፥ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ يُوسُفُ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ إِنِّي رَأَيْتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوْكَبًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ رَأَيْتُهُمْ لِي سَاجِدِينَ

ዩሡፍ እና "አሥራ አንድ ከዋክብት" ከተባሉት ጋር አሥራ ሁለት ናቸው፥ ዩሡፍ "አባቴ ሆይ" ያለው የአሥራ ሁለቱ ልጆች አባት ነው። ይህም አባት "የዕቁብ" ነው፦

12፥67 አለም «ልጆቼ ሆይ! በአንድ በር አትግቡ! ግን በተለዩ በሮች ግቡ»፡፡ وَقَالَ يَا بَنِيَّ لَا تَدْخُلُوا مِن بَابٍ وَاحِدٍ وَادْخُلُوا مِنْ أَبْوَابٍ مُّتَفَرِّقَةٍ
12፥68 አባታቸው ካዘዛቸው ስፍራ በገቡ ጊዜ ከአሏህ ፍርድ ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከለክልላቸው አልነበረም፥ ግን በ-"የዕቁብ" ነፍስ ውስጥ የነበረች ጉዳይ ናት፡፡ ፈጸማት፥ እርሱም ስላሳወቅነው የዕውቀት ባለቤት ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ وَلَمَّا دَخَلُوا مِنْ حَيْثُ أَمَرَهُمْ أَبُوهُم مَّا كَانَ يُغْنِي عَنْهُم مِّنَ اللَّهِ مِن شَيْءٍ إِلَّا حَاجَةً فِي نَفْسِ يَعْقُوبَ قَضَاهَا ۚ وَإِنَّهُ لَذُو عِلْمٍ لِّمَا عَلَّمْنَاهُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

"በተለዩ በሮች ግቡ" ብሎ ያዘዛቸው አባታቸው የዕቁብ ስለሆነ "በ-"የዕቁብ" ነፍስ ውስጥ የነበረች ጉዳይ ናት" ይለናል። የዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ፦ "ከእኔ በኋላ ማንን ታመልካላችሁ? ሲላቸው ልጆቹም፦ "አምላክህን እና የአባቶችህን የኢብራሂምን፣ የኢሥማዒልን፣ የኢሥሓቅን አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እናመልካለን፥ እኛ ለእርሱ ፍፁም ታዛዦች ነን" አሉ፦

2፥133 የዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ፦ "ከእኔ በኋላ ማንን ታመልካላችሁ? ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? እነርሱም፦ "አምላክህን እና የአባቶችህን የኢብራሂምን፣ የኢሥማዒልን፣ የኢሥሓቅን አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እናመልካለን፥ እኛ ለእርሱ ፍፁም ታዛዦች ነን" አሉ፡፡ أَمْ كُنتُمْ شُهَدَاءَ إِذْ حَضَرَ يَعْقُوبَ الْمَوْتُ إِذْ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعْبُدُونَ مِن بَعْدِي قَالُوا نَعْبُدُ إِلَـٰهَكَ وَإِلَـٰهَ آبَائِكَ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ إِلَـٰهًا وَاحِدًا وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

"ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ አሥራ ሁለቱ የየዕቁብ ልጆች አንዱን አምላክ በብቸኝነት የሚያመልኩት እንደነበር ይህ ጥቅስ በቂ አስረጅ ነው። የዕቁብ ነቢይ ነበር፦

19፥49 እነርሱን ከአሏህ ሌላ የሚያመልኩትን በራቀ ጊዜ ለእርሱ(ለኢብራሂም) ኢሥሓቅን እና የዕቁብን ሰጠነው፡፡ "ሁሉንም ነቢይ አደረግን"፡፡ فَلَمَّا اعْتَزَلَهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ وَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ ۖ وَكُلًّا جَعَلْنَا نَبِيًّا

"ሁሉን" ማለት አንቀጹ ላይ የተጠቀሱት ኢብራሂም፣ ኢሥሓቅ እና የዕቁብ ናቸው፥ አሏህ ሁሉንም ነቢይ አድርጓቸዋል። ስለዚህ ኢሥራኢል የዕቁብ ስለመሆኑ የቁርኣን፣ የሐዲስ እና የተፍሢር መረጃ እና ማስረጃ አቅርበናል፥ ኢሥራኢል የዕቁብ ስለመሆኑ ኢጅማዑል ዑለማእ ወጥ የሆነ ስምምነት"Consensus" አላቸው።

በመርፌ እና በወስፌ "ኢሥራኢል የዕቁብ ነው" የሚል ማስረጃ የለም" ብላችሁ ጮቤ ስትረግጡ የነበራችሁ ኩፋሮች ሆይ! የተማመናችሁበት ኮሰረት ከሴ እና አንካሴ የት አለ? ዲኑል ኢሥላም ጥንብ እርኩሱን እንዲወጣላችሁ እና ዶግ አመድ እንዲሆንላችሁ የማትቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማትፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማትደረምሱት መሬት እንደሌለ እሙን እና ቅቡል ቢሆንም ለዛሬው ግን አልተሳካላችሁም። አምላካችን አሏህ ለእናንተ ሂዳያውን ለእኛንም ኢሥቲቃማውን ይወፍቀን! አሚን። 

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም