በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ቁርኣን 2፥114 የአላህንም መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳ ከከለከለ እና እርሷንም በማበላሸት ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَاجِدَ اللَّهِ أَن يُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَن يَدْخُلُوهَا إِلَّا خَائِفِينَ ۚ لَهُمْ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ

የአክሱም መንግሥት ንጉሥ ካሌብ እስከ የመን ድረስ ይገዛ ነበር፥ በጃሂሊያህ ጊዜ የካሌብ ጦር መሪ አብረሃህ አል አሽረም ነበረ። በ 570 ድኅረ ልደት "አብረሃህ አል አሽረም" أَبْرَهَة ٱلْأَشْرَم እና ጭፍሮቹ የአሏህን ቤት ለማፍረስ በዝሆን ጋልበው ወደ መካ መጡ፥ አሏህም እነዚህን የዝሆን ባለቤቶችን ተንኮል በጥፋት ውስጥ ከንቱ አደረገ፦

ቁርኣን 105፥1 በዝሆኑ ባለቤቶች ጌታህ እንዴት እንደሠራ አላወቅህምን?
أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِأَصْحَابِ الْفِيلِ
ቁርኣን 105፥2 ተንኮላቸውን በጥፋት ውስጥ ከንቱ አላደረገምን?
أَلَمْ يَجْعَلْ كَيْدَهُمْ فِي تَضْلِيلٍ

አምላካችን አሏህ በእነርሱም ላይ ከተጠበሰ ጭቃ በኾነ ድንጋይ ማለትም በሸክላ”brick” የሚወረውሩባቸው መንጎች የኾኑን አዕዋፍን በመላክ ቅጠሉ እንደ ተበላ አዝመራም አደረጋቸው፦

ቁርኣን 105፥3 “በእነርሱም ላይ መንጎች የኾኑን አዕዋፍን ላከ”፡፡
وَأَرْسَلَ عَلَيْهِمْ طَيْرًا أَبَابِيلَ
ቁርኣን 105፥4 “ከተጠበሰ ጭቃ በኾነ ድንጋይ የምትወረውርባቸው የኾነችን አዕዋፍ”፡፡
تَرْمِيهِم بِحِجَارَةٍ مِّن سِجِّيلٍ
ቁርኣን 105፥5 “ቅጠሉ እንደ ተበላ አዝመራም አደረጋቸው”፡፡
فَجَعَلَهُمْ كَعَصْفٍ مَّأْكُولٍ

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቁረይሾች ጊዜ ሲቆጥሩ እራሱ “ዓሙል ፊል” عامُ الْفِيل ማለትም “የዝሆን ዓመት” እያሉ ነበር። ታላቁን የአሏህ ቤት መሥጂድ ለማፍረስ የቋመጠው የካሌብ ጦር መሪ አብረሃህ አል አሽረም ከሐበሻህ ምድር እንደነበር ልብ አድርግ! “አሏህ” “አሏህ” የሚል ሲጠፋ እና ቁርኣን ከሰዎች ልብ ሲወሰድ ከሐበሻህ የሚመጣ ሰው ዙ አሥ-ሡወይቀተይን የአሏህን ቤት ከዕባህን ያፈርሳል፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 82
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ከሐበሻህ የሆነ ዙ አሥ-ሡወይቀተይን ከዕባህን ያፈርሳል”።
أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ يُخَرِّبُ الْكَعْبَةَ ذُو السُّوَيْقَتَيْنِ مِنَ الْحَبَشَةِ ‏”‌‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 73
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ከሐበሻህ የሆነ ዙ አሥ-ሡወይቀተይን የአሏህ ዐዘ ወጀልን ቤት ያፈርሳል”።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ ذُو السُّوَيْقَتَيْنِ مِنَ الْحَبَشَةِ يُخَرِّبُ بَيْتَ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ ‏”‏ ‏

“ዙ አሥ-ሡወይቀተይን” ذُو السُّوَيْقَتَيْنِ ማለት “ባለ ሁለት ትንሽ ቅልጥም” ወይም “ባለ ሁለት አጭር ቅልጥም” ማለት ነው፥ በተንኮል የአሏህን ቤት አፍርሶ የከዕባን ሀብት ለማውጣት የሚፈልግ ይህ ሰው ነው።
ሐበሻውያንን የሸገር ከተማ አስተዳደር በሸገር ከተማ የአሏህ ቤት የሆኑትን መሣጂድ ማፍረሳቸው ልዩ ትርጉም አለው፥ ወደፊት ለሚመጣው "ዙ አሥ-ሡወይቀተይን" መንገድ እየጠረጉለት ነው። በምድር ላይ ያሉት መስጊዶች ሁሉ የአሏህ ብቻ ናቸው፥ በውስጣቸው ከአሏህ ጋር አንድንም አንገዛም። ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ እናወድሰዋለን፥ በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ እናጠራለን። መስጊዶች በውስጣቸው የአሏህ ስሙ እንዳይወሳ የሚከለክሉ እና መስጊዶች በማፈራረስ እንዳይገነባ ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው። ለእነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፦

ቁርኣን 2፥114 የአላህንም መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳ ከከለከለ እና እርሷንም በማበላሸት ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَاجِدَ اللَّهِ أَن يُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَن يَدْخُلُوهَا إِلَّا خَائِفِينَ ۚ لَهُمْ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ

መሥጂድ ሲያፈራርሱ እጃችሁን አጣምራችሁ እዩ አልተባለም። ነገር ግን ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቅዶልናል፦

ቁርኣን 22፥39 ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፡፡ አላህም እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡
أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

አንቀጹ ይቀጥልና ሲበደሉ ፍትሕ የሚያስተካክሉ አካላት ከሌሉ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖች፣ ምኩራቦች እና በውስጣቸው የአሏህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶች ይፈርሳሉ ይለናል፦

ቁርኣን 22፥40 ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት ተፈቀደ፡፡ ”አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም "በተፈረሱ" ነበር፡፡ አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡
الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَن يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ ۗ وَلَوْلَا دَفْعُ اللَّهِ النَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّهُدِّمَتْ صَوَامِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَاتٌ وَمَسَاجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا اسْمُ اللَّهِ كَثِيرًا ۗ وَلَيَنصُرَنَّ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

ስለዚህ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችን፣ ምኩራቦችን እና መስጊዶችን ማፍረስ ወሰን ማለፍ ነው። “አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! አንደኛው በሌላኛ ፍትሕ ለማስከበር መገፍተሩ ማለትም መጋደል ከሌለ ወሰን አላፊዎች ምድሩቱን ያበላሻሉ፦

ቁርኣን 2፥190 እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

"በአላህ መንገድ ተጋደሉ" የሚለው ይሰመርበት! በአሏህ መንገድ ለአሏህ ብሎ ጅሁድ ማድረግ ከዘውግ፣ ከብሔር፣ ከፓለቲካ የጸዳ እና ከስሜታዊነት የጸዳ ነው። ስለዚህ የሸገር ከተማ አስተዳደር አርፎ ካልተቀመጠ በመላው ሙሥሊም ተደራጅቶ መጋደል አለበት! ለዚህ ጅሁድ በነሲብ፣ በስሜት፣ በጭፍን ሳይሆን በሐልዮ፣ በአርምሞ፣ በነቢብ እና በገቢር ምክክር ያስፈልጋል። መሣጂድን የሚያፈርሱትን አሏህ በዱንያ ላይ ቅጣታቸውን ያሳየን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም