አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

"ማዳን እና መዳን በኢሥላም" በሚል የተጻፈው ይህ መጽሐፍ በክርስትና እና በኢሥላም ያለውን የነገረ ድኅነትን ነጥብ በሃይማኖት ንጽጽር የሚያቀርብ መጽሐፍ ነው፥ ኲታ ገጠም በሆኑ ነጥቦት እና ግራ እና ቀኝ ያማከል ውል ያለ ሙግት በውስጡ ለማካተት ሞክረናል።

የመዳን አቀማመጥ"Deposit of Salvation" ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ደርዝ እና ፈርጅ ባለው መልኩ የተቀመጠ ደማቅ አዋጅ"Bold Claim" ነው፥ ማንም ሚሽነሪ ተነስቶ "ኢየሱስ ያድናል" በማለት የኩፍር እና የሺርክ ጎጆ ሠርቶ የጀሀነምን እንቁላል አይፈለፍላትም። ጤዛ በመላስ፣ ድንጋይ በመንተራስ፣ አመድ በመነስንስ፣ ማቅ በመልበስ፣ ሰብቅ በመቅመስ መዳን የለም። ሰዎችን ወደ አሏህ መጣራት የማዳን ሥራ"Economy of Salvation" ነው፥ ሐቅን በማቀንቀን ባጢልን በመቀናቀን አብዮት የሚያስነሳ አብዮተኛ ትውልድ እንዲያስነሳ ሆን ተብሎ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው። ኢንሻ አሏህ!

መጽሐፉን የምትፈልጉ አገር ውስጥ ያላችሁ ሆነ ከአገር ውጪ ያላችሁ በ +251928444408 ዐብዱ መርካቶ ብላችሁ በቀጥታ አሊያም በዋትሳፕ ታገኙታላችሁ፥ እንዲሁ በቴሌ ግራም ይህንን ዩዘር ኔም በመጠቀም http://t.me/merkatozon ማግኘት ትችላላችሁ።

መጽሐፉን አንብቡ አስነብቡ! ለብዙዎች ሠበቡል ሂዳያህ ለመሆን ሁሉም ቦታ በማጋራት የዳዕዋ አድማሱን ያስፉ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!