በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 7፥180 ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ ስትጸልዩ በእርሷም ጥሩት! እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተዋቸው፡፡ ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ፡፡
وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا ۖ وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ ۚ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
አምላካችን አሏህ ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰሉ "አል-አሥ ማኡል ሑሥና" الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ማለትም "የተዋቡ ስሞች" አሉት፦
ቁርኣን 20፥8 አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አሉት፡፡
اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
ቁርኣን 7፥180 ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ ስትጸልዩ በ-"እርሷም" ጥሩት! እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተዋቸው፡፡ ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ፡፡
وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا ۖ وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ ۚ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
"እርሷ" ለሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም የገባው "ሃ" هَا ሲሆን "አሥማእ" أَسْمَاء የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ነው፥ ሙአነስ አንዳንዴ ጀምዕን ለማመልከት እንደሚመጣ በነሕው ደርሥ ግልጽ ነው። ነገር ግን ቁሬይሾች የአሏህ ስሞችን በማጣመም ነፍሶች የሚዘነበሉበትን ጥርጣሬ ተከትለዋል፥ "አሏህ" اللَّه ከሚለው ስም "ላት" لَّات በማለት፣ "ዐዚዝ" عَزِيزِ ከሚለው ስም "ዑዛ" عُزَّىٰ በማለት፣ "መናን" مَنَّان ከሚለው ስም "መናት" مَنَاة በማለት አጣመዋል፦
ቁርኣን 53፥19 ላትን እና ዑዛን አያችሁን?
أَفَرَأَيْتُمُ اللَّاتَ وَالْعُزَّىٰ
ቁርኣን 53፥20 ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን አያችሁን?
وَمَنَاةَ الثَّالِثَةَ الْأُخْرَىٰ
፨የመጀመሪያይቱ ጣዖት በግሪክ "አቴና" በሮም "ሚነርቫ" በከነዓን "አናት" በግብጽ "ኔዝ" ትባል ነበር፥ ይህቺ የጥበብ፣ የእጅ ሥራ፣ የፍትሕ፣ የሕግ፣ የድል አምላክ ተብላ የምትጠራውን ጣዖት ወደ ጧዒፍ ከተማ በወጅ ሸለቆ አምጥተው ስሟን "አሏህ" اللَّه ከሚለው ስም በማጣመም "ላት" لَّات አሏት። ላት በላይዋ ላይ የተቀረጹ ጽሑፎች ያሏ ነጭ ድንጋይ ነበረች፥ ላት ብለው በአንስታይ የሰየሟት ጣዖት ጥንት በአሏህ ቤት ሐጅ ለሚያደርጉ ሑጃጅ የገብስ ሾርባ የሚያቀርብ ሷሊሕ ሰው ሲሆን እርሱ ሲሞት እሳቤውን ከፓጋን በመውሰድ በእርሱን መቃብር ማምለክ ጀመሩ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 380
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ላት እና ዑዛ" ስለሚለውን ንግግር፦ "ላት ለሐጅ ሰዎች የገብስ ሾርባ የሚያቀርብ ሰው ነበር" አለ።
عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، رضى الله عنهما فِي قَوْلِهِ {اللاَّتَ وَالْعُزَّى} كَانَ الَّلاَتُ رَجُلاً يَلُتُّ سَوِيقَ الْحَاجِّ.
ይህቺን ጣዖት በ 9 የሒጅራህ አቆጣጠር ወይም በ 630 የጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በጥቅም ወር ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" አቡ ሡፍያን ኢብኑ ሐርብን እና አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባህን ልከዋቸው አፈራርሰዋታል።
፨ሁለተኛይቱን በከነዓን "አስታሮት" በባቢሎን "ኤሽታር" በሮም "ቬኑስ" በግሪክ "አፍሮዳይት" በግብጽ "አዞር" ትባል ነበር፥ ይህቺ የጦርነት፣ የፍቅር፣ የአደን አምላክ ተብላ የምትታመን ጣዖትን በመካህ እና በጧዒፍ መካከል ባለው በነኽላህ አምጥተው ስሟን "ዐዚዝ" عَزِيزِ ከሚለው ስም በማጣመም "ዑዛ" عُزَّىٰ አሏት። ዑዛ በመጋረጃ የተኖረች እና በመታሰቢያ ሐውልት የተለወሰች ዛፍ ነበረች፥ በ 8 የሒጅራህ አቆጣጠር ወይም በ 630 የጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በጥር ወር ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ኻሊድ ኢብኑል ወሊድን ልከውት ዑዛ የተባለችውን ጣዖት አፈራርሷል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 11, ሐዲስ 8
ሠዕድ እንደተረከው፦ ስለ ላት እና ዑዛ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከአሏህ በቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም፥ ለእርሱ አንድም ተጋሪ የለውም"።
عَنْ سَعْدٍ، قَالَ حَلَفْتُ بِاللاَّتِ وَالْعُزَّى فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ " قُلْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ
፨ሦስተኛይቱ በመካህ እና በመዲናህ መካከል በሚገኘው በሙሸለል አካባቢ የምትመለከው የእጣ፣ የዕድል፣ የጊዜ እና የመዳረሻ አምላክ ተብላ የምትታመነበው የነበረችው መናት ከላት እና ዑዛ በፊት የነበረች ስትሆን ስሟን "መናን" مَنَّان ከሚለው ስም በማጣመም "መናት" مَنَاة አሏት። "ሐናን" حَنَان ማለት "ርኅራኄ" ማለት ሲሆን ከአሏህ የሚሰጥ ነው፦
ቁርኣን 19፥13 ከእኛም የሆነን ርኅራኄ ንጽሕናንም ሰጠነው፡፡ ጥንቁቅም ነበር፡፡
وَحَنَانًا مِّن لَّدُنَّا وَزَكَاةً ۖ وَكَانَ تَقِيًّا
እዚህ አንቀጽ ላይ "ርኅራኄ" ለሚለው የገባው ቃል "ሐናን" حَنَان ነው። "አል-መናን" الْمَنَّان ደግሞ "ርኅራኄ ሰጪ" ማለት ሲሆን በሐዲስ የተገለጸ የአሏህ ስም ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 32
Iአነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንድ ሰው(ጂብሪል)፦ "አሏህ ሆይ! በእውነት በጎነት ምስጋና ሁሉ ለአንተ እንዲሆን እለምንሃለው፥ ከአንተ በቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም፥ ለአንተ አንድም ተጋሪ የለህም። አንተ አል-መናን፣ የሰማያት እና የምድር አስገኚ፣ የግርማ እና የክብር ባለቤት ነህ" ሲል ሰምቻለው"።
عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ سَمِعَ النَّبِيُّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ رَجُلاً يَقُولُ اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ بِأَنَّ لَكَ الْحَمْدَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ وَحْدَكَ لاَ شَرِيكَ لَكَ الْمَنَّانُ بَدِيعُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضِ ذُو الْجَلاَلِ وَالإِكْرَامِ"
በ 8 የሒጅራህ አቆጣጠር ወይም በ 630 የጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ሠዒድ ኢብኑ ዘይድ አል-አሽሀሊይን ልከውት መናህ የተባለችውን ይህቺን ጣዖት አፈራርሷል።
እነዚህ ዐረብ ጣዖታውያን "መላእክት የአሏህ ሴቶች ልጀች ናቸው" በማለት መላእክትን ሴቶች በማድረግ ለአሏህ የማይገባውን ነገር ተናገሩ፦
ቁርኣን 53፥27 እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡
إِنَّ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ لَيُسَمُّونَ الْمَلَائِكَةَ تَسْمِيَةَ الْأُنثَىٰ
ቁርኣን 37፥150 ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?
أَمْ خَلَقْنَا الْمَلَائِكَةَ إِنَاثًا وَهُمْ شَاهِدُونَ
ቁርኣን 43፥19 መላእክትንም እነርሱ የአልረሕማን ባሮች የኾኑትን ሴቶች አደረጉ፡፡ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትጻፋለች፡፡ ይጠየቃሉም፡፡
وَجَعَلُوا الْمَلَائِكَةَ الَّذِينَ هُمْ عِبَادُ الرَّحْمَـٰنِ إِنَاثًا ۚ أَشَهِدُوا خَلْقَهُمْ ۚ سَتُكْتَبُ شَهَادَتُهُمْ وَيُسْأَلُونَ
ቁርኣን 17፥40 ጌታችሁ በወንዶች ልጆች መረጣችሁ እና ከመላእክት ሴቶችን ልጆች ያዝን? እናንተ ከባድን ቃል በእርግጥ ትናገራላችሁ፡፡
أَفَأَصْفَاكُمْ رَبُّكُم بِالْبَنِينَ وَاتَّخَذَ مِنَ الْمَلَائِكَةِ إِنَاثًا ۚ إِنَّكُمْ لَتَقُولُونَ قَوْلًا عَظِيمًا
ቁርኣን 16፥57 ለአላህም ከመላእክት ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ። ጥራት ተገባው፡፡ ለእነርሱም የሚፈልጉትን ወንዶች ልጆችን ያደርጋሉ፡፡
وَيَجْعَلُونَ لِلَّهِ الْبَنَاتِ سُبْحَانَهُ ۙ وَلَهُم مَّا يَشْتَهُونَ
ከእነርሱ አንዳቸው ግን ለአልረሕማን ምሳሌ ባደረጉለት ነገር በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል፥ ነገር ግን ለአሏህ መላእክትን ሴቶች ልጆች በማድረግ በአሏህ ላይ ቀጠፉ፦
ቁርኣን 43፥16 ከሚፈጥረው ውስጥ ሴቶች ልጆችን ያዘን? በወንዶች ልጆችም እናንተን መረጣችሁን?
أَمِ اتَّخَذَ مِمَّا يَخْلُقُ بَنَاتٍ وَأَصْفَاكُم بِالْبَنِينَ
ቁርኣን 52፥39 ወይስ ለእርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን? ለእናንተም ወንዶች ልጆች አሏችሁን?
أَمْ لَهُ الْبَنَاتُ وَلَكُمُ الْبَنُونَ
ቁርኣን 16፥58 አንዳቸውም በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል፡፡
وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِالْأُنثَىٰ ظَلَّ وَجْهُهُ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ
ቁርኣን 43፥17 አንዳቸውም ለአልረሕማን ምሳሌ ባደረጉለት ነገር በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ በቁጭት የተመላ ኾኖ ፊቱ የጠቆረ ይኾናል፡፡
وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِمَا ضَرَبَ لِلرَّحْمَـٰنِ مَثَلًا ظَلَّ وَجْهُهُ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ
እነርሱ ወንድ ልጅ ሲወለድ ለራሳቸው ደስ ሲላቸው በተቃራኒው ሴት ስትወለድ የሚከፋቸው ሲሆን ለአሏህ መላእክትን ሴቶች ልጆች ማድረጋቸው አድሏዊ ንግግር ነው፥ አሏህም፦ "ለእናንተ ወንድ ልጅ ለእርሱም ሴት ልጅ ይኖራልን? ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት" በማለት መልስ ሰጣቸው፦
ቁርኣን 53፥21 ለእናንተ ወንድ ልጅ ለእርሱም ሴት ልጅ ይኖራልን?
أَلَكُمُ الذَّكَرُ وَلَهُ الْأُنثَىٰ
ቁርኣን 53፥22 ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት፡፡
تِلْكَ إِذًا قِسْمَةٌ ضِيزَىٰ
እነዚህን ጣዖታት ሙሽሪኮች እና አባቶቻቸው "ላት፣ ዑዛ እና መናህ" ብለው የሰየሟቸው ስሞች እንጂ መጥቀም ሆነ መጉዳት የሚችሉ አይደሉም፥ አሏህን ሰዎች እነዚህን ጣዖታት እንዲያመልኩ ማስረጃ አላወረደም፦
ቁርኣን 53፥23 እነርሱንም እናንተ እና አባቶቻችሁ የሰየማኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፥ አላህ በእርሷ ምንም ማስረጃ አላወረደም።
إِنْ هِيَ إِلَّا أَسْمَاءٌ سَمَّيْتُمُوهَا أَنتُمْ وَآبَاؤُكُم مَّا أَنزَلَ اللَّهُ بِهَا مِن سُلْطَانٍ
"አህዋእ" أَهْوَآء ማለት "ዝንባሌ"inclination" ማለት ነው፥ ይህ ዝንባሌ ከነፍሢያህ ሲሆን አሏህን ሰዎች እነዚህን ጣዖታት እንዲያመልኩ ማስረጃ ያላወረደበትን ነገር በዝንባሌአቸው ጥርጣሬን እንዲከተሉ ሆነዋል፥ በእርግጥም ከአሏህ ዘንድ የመጣው መመሪያ ቁርኣን አሏህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት የመጣ ነው፦
ቁርኣን 53፥23 ነፍሶች የሚዘነበሉበትን ጥርጣሬን እንጅ ሌላ አይከተሉም፥ በእርግጥ ከጌታቸውም መምሪያ መጥቶላቸዋል።
إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَمَا تَهْوَى الْأَنفُسُ ۖ وَلَقَدْ جَاءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ الْهُدَىٰ
ቁርኣን 45፥11 ይህ ቁርኣን መመሪያ ነው፡፡ እነዚያም በጌታቸው አንቀጾች የካዱት ለእነርሱ ከብርቱ ቅጣት የኾነ አሳማሚ ስቃይ አላቸው፡፡
هَـٰذَا هُدًى ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ لَهُمْ عَذَابٌ مِّن رِّجْزٍ أَلِيمٌ
ቁርኣን 14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰጹበት የተወረደ ነው፡፡
هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ
አምላካችን አሏህ በተውሒድ የምንጸና ሙዋሒድ ያርገን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም