በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 39፥42 አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፡፡
ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا
አሏህ ሩሓችንን በእንቅልፏ ጊዜ ሲወስዳት ያለ ውጫዊ ነገር በውሳጣዊ ነገር ታያለች፣ ትሰማለች፣ ትሄዳለች፣ ትናገራለች፥ የሕልም ዓለም ሩሕ ከአካል ከተለየች በኃላ ያለውን ሕይወት ማሳያ ናሙና ነው። አምላካችን አሏህ በሌሊት ይወስደናል፥ ከዚያም በቀን ይቀሰቅሰናል፦
ቁርኣን 6፥60 "እርሱም ያ በሌሊት "የሚወስዳችሁ" በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ "የሚቀሰቅሳችሁ" ነው"፡፡
وَهُوَ الَّذِي يَتَوَفَّاكُم بِاللَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِالنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰ أَجَلٌ مُّسَمًّى
"የሚወስዷችሁ" ለሚለው የገባው ቃል "የተወፋኩም" يَتَوَفَّاكُم ሲሆን "የሚያስተኛችሁ" ማለትም ነው። አምላካችን አሏህ በቀን ደግሞ ይቀሰቅሰናል፥ "በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው" የሚለው ይሰመርበት! አሏህ ሩሓችንን በእንቅልፍ ጊዜ ወስዶ በንቃት ጊዜ ይመልሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 97
አቡ ቀታዳህ እንደተረከው፦ "ከሶላት ሰዎች በተኙ ጊዜ የአሏህ ነቢይም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ በሚሻው ጊዜ ሩሓችሁን ይወስዳል፥ በሚሻው ጊዜ ይመልሳል"።
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي قَتَادَةَ، عَنْ أَبِيهِ، حِينَ نَامُوا عَنِ الصَّلاَةِ، قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم " إِنَّ اللَّهَ قَبَضَ أَرْوَاحَكُمْ حِينَ شَاءَ، وَرَدَّهَا حِينَ شَاءَ "
ሰው የመንፈስ እና የአካል ሁለትዮች"bi-partite" ቀዋሚ ማንነት ሲሆን አካሉ በሌሊት እንቅልፍ እንደሚያርፍ እና በቀን እንደሚቀሰቀስ ሁሉ በሞትን ጊዜ አካሉ በትልቁ እንቅልፍ ያርፍ እና በትንሳኤ ቀን ይቀሰቀሳል፦
36፥51 በቀንዱም ይነፋል፥ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ፡፡
وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ
36፥52 «ወይ ጥፋታችን! ከእንቅልፋችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን እና መልእክተኞቹ እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡
قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ
እንቅልፍ ሩሕ እና አካል የሚለያዩበት ስለሆነ የሞት ወንድም ተብሏል፥ እንቅልፍ ትንሹ ሞት ስለሆነ ለዛ ነው የምሽት ዚክር ላይ "አሏህ ሆይ! በስምህ እሞታለው ሕያው እሆናለው" የንጋት ዚክር ላይ ደግሞ፦ "ለአሏህ ምስጋና ይሁን! ለዚያ ከአሞተን በኃላ ሕያው ላደረገን፥ መቀስቀስም ወደ እርሱ ነው" የምንለው፦
አል-ሙጀመል አውሠጥ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 938
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "የአሏህ ነቢይም"ﷺ" እንዲህ ተጠየቁ፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! የጀናህ ባለቤቶች ይተኛሉን? የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "እንቅልፍ የሞት ወንድም ነውና የጀናህ ባለቤቶች አይተኙም"።
عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ سُئِلَ نَبِيُّ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَيَنَامُ أَهْلُ الْجَنَّةِ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ النَّوْمُ أَخُو الْمَوْتِ وَأَهْلُ الْجَنَّةِ لا يَنَامُونَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 23
ሑዘይፋህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ወደ አልጋቸው በሄዱ ጊዜ፦ "አሏህ ሆይ! በስምህ እሞታለው ሕያው እሆናለው" ይሉ ነበር፥ በነቁ ጊዜ፦ "ለአሏህ ምስጋና ይሁን! ለዚያ ከአሞተን በኃላ ሕያው ላደረገን፥ መቀስቀስም ወደ እርሱ ነው"።
عَنْ حُذَيْفَةَ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِذَا أَوَى إِلَى فِرَاشِهِ قَالَ " اللَّهُمَّ بِاسْمِكَ أَحْيَا وَأَمُوتُ ". وَإِذَا أَصْبَحَ قَالَ " الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَحْيَانَا بَعْدَ مَا أَمَاتَنَا وَإِلَيْهِ النُّشُورُ "
"ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል" ማለት ሩሕ በእንቅልፍ ጊዜ መወሰዷን ሲያመለክት "አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል" ማለት ደግሞ በሞት ጊዜ አካል ወደ አፈር ሲመለስ ሩሕ ወደ አሏህ ይወሰዳል፦
ቁርኣን 39፥42 አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፡፡
ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا
እዚህ አንቀጽ ላይ "ይወስዳል" ለሚለው የገባው ቃል "የተወፈ" يَتَوَفَّى ሲሆን አሏህ መለኩል መውትን በመላክ ነፍስን ይወስዳል፦
ቁርኣን 32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ይወስዳችኋል፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡
قُلْ يَتَوَفَّاكُم مَّلَكُ الْمَوْتِ الَّذِي وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ
"የተወፋኩም" يَتَوَفَّاكُم ማለት "ይወስዳችኋል" ማለት ሲሆን "መለኩል መውት" مَلَكُ المَوت ማለት "መልአከ ሞት" ወይም "የሞት መልአክ" ማለት ነው። "ሞት" የሚለው ቃል ተዛራፊ እንጂ ባለቤትን አያመለክትም፥ መልአከ ሞት የሚባሉት መላእክት ብዙ ናቸው፦
6፥61 አንዳችሁንም ሞት በመጣበት ጊዜ የሞት መልእክተኞቻችን እነርሱ ትእዛዛትን የማያጓድሉ ሲኾኑ ይወስዱታል፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ تَوَفَّتْهُ رُسُلُنَا وَهُمْ لَا يُفَرِّطُونَ
እነዚህ የሞት መላእክት በጥቅሉ "አን ናዚዓት" እና "አን-ናሺጧት" ይባላሉ፥ "አን ናዚዓት" النَّازِعَات ማለት "በኃይል ወሳጆች" "ሩሕን ከአካል በኃይል አውጪዎች" ማለት ሲሆን አን-ናዚዓት በመባል የሚታወቁት የሞት መላእክት የከሓድያንን ሩሕ በኃይል አውጪዎች ናቸው። አን ናዚዓት ከሓድያንን የሚወስዷቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ "ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ?» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፥ እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በራሳቸው ላይ ይመሰክራሉ፦
ቁርኣን 79፥1 በኃይል አውጪዎች በኾኑት"።
وَالنَّازِعَاتِ غَرْقًا
ቁርኣን 7፥37 የሞት መልእክተኞቻችንም "የሚወስዷቸው" ኾነው በመጡባቸው ጊዜ «ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ?» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፡፡ እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በራሳቸው ላይ ይመሰክራሉ፡፡
حَتَّىٰ إِذَا جَاءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوا أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ قَالُوا ضَلُّوا عَنَّا وَشَهِدُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا كَافِرِينَ
ቁርኣን 8፥50 መላእክት እነዚያንም የካዱትን ፊቶቻቸውን እና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» እያሉ በሚወስዷቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር፡፡
وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ يَتَوَفَّى الَّذِينَ كَفَرُوا ۙ الْمَلَائِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَارَهُمْ وَذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيقِ
"አን-ናሺጧት" النَّاشِطَات ማለት "በቀስታ ወሳጆች" "ሩሕን ከአካል በቀስታ መዘማዦች" ማለት ሲሆን አን-ናሺጧት በመባል የሚታወቁት የሞት መላእክት የአማንያንን ሩሕ በቀስታ አውጪዎች ናቸው። አን-ናሺጧት አማንያንን፦ "ሰላም በእናንተ ላይ" እያሉ የሚወስዷቸው ናቸው፡፡ "ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ" ይባላሉ፦
ቁርኣን 79፥2 "በቀስታ መምዘዝንም መዘማዦች በኾኑት"።
وَالنَّاشِطَاتِ نَشْطًا
ቁርኣን 16፥32 እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚወስዷቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» ይባላሉ፡፡
الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ طَيِّبِينَ ۙ يَقُولُونَ سَلَامٌ عَلَيْكُمُ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
ከሞት በኃላ ሩሕ ሲወሰድ የሞት መላእክት እና ሩሓችን መነጋገራቸው በራሱ ሩሕ በሞት ጊዜ የሚወሰድ እንጂ ከአካል ጋር በአፈር የሚበሰብስ አለመሆኑን በቂ ማሳያ ነው። አምላካችን አሏህ "ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ" ከሚላት የጀነት ባለቤቶች ያድርገን! አሚን።
✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም