በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ቁርዓን 22፥26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩት፣ ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱት እና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» ባልነው ጊዜ አስታውስ
وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

“ሓጅ” حَآجّ ወይንም “ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት”pilgrimage” ማለት ነው፤ “ሐጅ” መደበኛ ዐብይ ጉብኝት ሲሆን “ዑምራ” عُمْرَة ደግሞ መደበኛ ያልሆነ ንዑስ ጉብኝት ነው፦

2፥196 ሐጅን እና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ
وَأَتِمُّوا الْحَجَّ وَالْعُمْرَةَ لِلَّه
3፥97 በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አለ፡፡ ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል፡፡ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደ እርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡
فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَّقَامُ إِبْرَاهِيمَ وَمَن دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
2፥158 ሶፋና መርዋ ከአላህ ምልክቶች ናቸው፤ “ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ” ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡
إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِن شَعَائِرِ اللَّهِ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَا

“የጎበኘ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐጀ” حَجَّ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ሐጅ የራሱ ጊዜ አለው፦

2፥89 ከለጋ ጨረቃዎች መለዋወጥ ይጠየቁሃል፡፡ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው፡፡
يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج
2፥197 ሐጅ ጊዜያቱ የታወቁ ወሮች ናቸው፡፡ በእነርሱም ውስጥ ሐጅን እንዲሠራ ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም፡፡
الْحَجُّ أَشْهُرٌ مَّعْلُومَاتٌ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ الْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي الْحَج
22፥28 ለእነርሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ ይመጡልሃል፡፡ ከእርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡
لِّيَشْهَدُوا۟ مَنَٰفِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ فِىٓ أَيَّامٍۢ مَّعْلُومَٰتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّنۢ بَهِيمَةِ ٱلْأَنْعَٰمِ فَكُلُوا۟ مِنْهَا وَأَطْعِمُوا۟ ٱلْبَآئِسَ ٱلْفَقِيرَ
89፥2 በዐሥር ሌሊቶችም እምላለው፡፡
وَلَيَالٍ عَشْرٍۢ

የታወቁ ቀኖች 12ኛ ወር- ዙል-ሒጃህ ላይ የመጀመሪያዎቹ ዐሥሩ ሌሊቶች ናቸው። አላህ በዚህ ወቅት ቤቱን እንዲጎበኙ ያዘዘው ለኢብራሂም ነው፦

22፥27 አልነውም፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና፡፡
وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ
22፥26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩት፣ ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱት እና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» ባልነው ጊዜ አስታውስ፡፡
وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

“ለሚዞሩት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሊጧዒፊነ” لِلطَّائِفِينَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ “ጠዋፍ” طَواف የሚለው ቃል “ጧፈ” طَافَ ማለትም “ዞረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዙረት” ማለት ነው፤ ቤቱን በመጎብኘት ሰባት ጊዜ መዞር አምላካችን አላህ ለኢብራሂም የሰጠው ትእዛዝ ነው፦

22፥29 ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላቸውንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፡፡ ስለቶቻቸውንም ይሙሉ፤ በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ፡፡
ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ

“ይዙሩ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የጠወፉ” يَطَّوَّفُوا  መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ቤቱን የሚዞሩት ዘዋሪዎች ደግሞ “ጧዒፍ” طَآئِف ይባላሉ፦

2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻ እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂም እና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ”፣ ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡
وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

ለኢብራሂም በመጀመሪያ አገናዛቢ መደብ “ቤቴን” የሚለው የሚለው የዓለማቱ ጌታ አላህ እንደሆነ ልብ አድርግ፤ ቁሬሾች በሶፋ እና በመርዋ መካከል ይጎበኙ ስለነበር የአንሷር ሰዎች በዛ ቦታ ጠዋፍ ማድረግ በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረ ሥርዓት አድርገው ያስቡ ነበር፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 129
ዓሲም እንደተረከው፦ ”እኔ አነሥ ኢብኑ ማሊክን”ረ.ዐ”፦ “በሶፋ እና በመርዋ መካከል መዞርን ትጠላ ነበርን? ብዬ ጠየኩት፤ እርሱም፦ አዎ! አላህ፦ “ሶፋና መርዋ ከአላህ ትዕዛዝ መፈጸሚያ ምልክቶች ናቸው፡፡ ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም” የሚለው አንቀጽ እስከሚያወርድ ድረስ በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረ ሥርዓት አርገን እናስብ ነበር
أَخْبَرَنَا عَاصِمٌ، قَالَ قُلْتُ لأَنَسِ بْنِ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ أَكُنْتُمْ تَكْرَهُونَ السَّعْىَ بَيْنَ الصَّفَا وَالْمَرْوَةِ قَالَ نَعَمْ‏.‏ لأَنَّهَا كَانَتْ مِنْ شَعَائِرِ الْجَاهِلِيَّةِ، حَتَّى أَنْزَلَ اللَّهُ ‏{‏إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِنْ شَعَائِرِ اللَّهِ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلاَ جُنَاحَ عَلَيْهِ أَنْ يَطَّوَّفَ بِهِمَا‏}‌‏.‏

“ኢሕራም” إحرام ማለት ቋንቋዊ ፍቺው “ክልክል” ማለት ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ በሐጅ እና በዑምራ ያለውን የቅድስና ሁኔታ ያመለክታል፤ በኢሕራም ውስጥ የሚገባው ሰው ሙሕሪም” محرم ይባላል። ሙሽሪኮች ሶፋና መርዋ መካከል መናት የሚባለውን ጣዖት አስገብተው ያመልኩ ነበር፣ ይህን የተረዱት የመዲና ሰዎች ኢሕራም የማናት ስም ይመስላቸው ነበር፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 4861
ዑርዋ እንደተረከው፦ ”እኔም ዓኢሻን”ረ.ዐ.” ስለ ሶፋና መርዋ ጠየኳት፤ እርሷም፦ “መናት የምትባለው ጣዖት በሙሸለል ተቀምጦ ነበር፤ ኢሕራም የእርሱ ስም ስለሚመስላቸው በሶፋ እና በመርዋ መካከል ጠዋፍ የማያረጉ ነበሩ። አላህም፦ “ሶፋና መርዋ ከአላህ ትዕዛዝ መፈጸሚያ ምልክቶች ናቸው” የሚለውን አንቀጽ አወረደ፤ ስለዚህ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እና ሙስሊሞች ጠዋፍ ያረጉ ጀመር
سَمِعْتُ عُرْوَةَ، قُلْتُ لِعَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ فَقَالَتْ إِنَّمَا كَانَ مَنْ أَهَلَّ بِمَنَاةَ الطَّاغِيَةِ الَّتِي بِالْمُشَلَّلِ لاَ يَطُوفُونَ بَيْنَ الصَّفَا وَالْمَرْوَةِ، فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِنْ شَعَائِرِ اللَّهِ‏}‏ فَطَافَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَالْمُسْلِمُونَ‏.‏

ሚሽነሪዎች፦ “ሐጅን የጀመሩት ፓጋን ዐረቦቹ ናቸው” የሚሉት የቡና ወሬ አላቸው። ሐጅ እና በውስጥ ያሉት ቅድመ-ተከተል አምላካችን አላህ ለነቢዩ ኢብራሂ ያዘዘው ሥርዓት እንደሆነ በአንክሮትና በአጽንዖት ከላይ አይተናል፤ ከዘመነ-ጃህሊያህ ሥርዓት ወስዶ ዐቂደቱል ረባንያ በሆነው በዲነል ኢስላም ላይ መጨመር ቢድዓም ሺርክም እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን፤ አላህ ዘንድ ከተጠሉት ክፉ አድራጊዎች ሁለተኛው ከዘመነ-ጃህሊያህ ሥርዓት ወስዶ ዲነል ኢስላም ላይ መጨመር መሆኑን ሐዲሳች ላይ በግልጽና በማያሻማ ተቀምጧል፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 87 ሐዲስ 21
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነብዩም፦ “ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”አላህ ዘንድ የተጠሉ ሦስት ሰዎች አሉ፦ አንደኛው ከትክክለኛው ግብረገብ ወጥቶ ክፉ ነገር አድራጊ፣ ሁለተኛው ከዘመነ-ጃህሊያህ ሥርዓት ኢስላም ውስጥ ለማስቀረት የሚፈልግ፣ ሦስተኛው ያለ ሕግ የአንድ ሰው ደም ማፍሰስ የሚፈልግ
عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ أَبْغَضُ النَّاسِ إِلَى اللَّهِ ثَلاَثَةٌ مُلْحِدٌ فِي الْحَرَمِ، وَمُبْتَغٍ فِي الإِسْلاَمِ سُنَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ، وَمُطَّلِبُ دَمِ امْرِئٍ بِغَيْرِ حَقٍّ لِيُهَرِيقَ دَمَهُ ‏

አምላካችን አላህ ቤቱን ከሚጎበኙት ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

✍️ከወንድም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም