በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 17፥64 ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል፡፡
وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ
“ዐዝፍ” عَزْف የሚለው ቃል “ዐዘፈ” عَزَفَ ማለትም “ሞዘቀ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ሙዚቃ” ማለት ነው፥ የሙዚቃ መጫወቻ በነጠላ “ሚዕዘፍ” مِعْزَف ሲባል በብዜት “መዓዚፍ” مَعَازِف ይባላል። ሸይጧን በድምፁ ሰዎችን የሚወሰውሰው እና የሚነሽጠው በዘፈን እና በሙዚቃ መሣሪያ ነው፦
ቁርኣን 17፥64 ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል፡፡
وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ 17፥64
"ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል" በድምፅህ ሲል በሙዚቃ መሣሪያ ድምፅ፣ በዘፈን ድምፅ እና በሌላ አጸያፊ ነገር ማለቱ ነው"።
{ مَنِ ٱسْتَطَعْتَ مِنْهُمْ بِصَوْتِكَ } بدعوتك ويقال بصوت المزامير والغناء وسائر المناكير.
"ጀረሥ" جَرَس የሚለው ቃል "ጀረሠ" جَرَسَ ማለትም "ደወለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ደውል" ማለት ነው፥ "አጅራሥ" أَجْرَاس ደግሞ የጀረሥ ብዙ ቁጥር ሲሆን አጠቃላይ የሙዚቃ መሣሪያን የሚወክል ነው። ጀረስ የሸይጧን መዝሙር ነው፥ የሙዚቃ መሣሪያ ያለበት ቤት መላእክት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 159
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ጀረሥ የሸይጧን መዝሙር ነው”።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ “ الْجَرَسُ مَزَامِيرُ الشَّيْطَانِ
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 36 , ሐዲስ 18
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ “የአላህ መልክተኛም”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ ”መላእክት ጀረሥ ያለበት ቤት አይገቡም”።
وَقَالَتْ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ “ لاَ تَدْخُلُ الْمَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ جَرَسٌ
እዚህ ድረስ ከተግባባን ጎትቶ ጎትጉቶ በአንድ ቋት ውስጥ የመፈረጅ አባዜ የተጠናወታቸው ሚሽነሪዎች ያቀረቡትን ሐዲስ ማየት ይቻላል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 1 , ሐዲስ 2
የምእመናን እናት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ ሓሪሥ ኢብኑ ሂሻም"ረ.ዐ." የአሏህ መልእክተኛን"ﷺ" እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፥ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ሆይ! ወሕይ እንዴት ነው የሚመጣልዎት? ብሎ ጠየቃቸው፥ የአሏህ መልክተኛም”ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንዳንድ ጊዜ “እንደ” ደወል ድምፅ ይመጣኛል"።
عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ الْحَارِثَ بْنَ هِشَامٍ ـ رضى الله عنه ـ سَأَلَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ يَأْتِيكَ الْوَحْىُ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ أَحْيَانًا يَأْتِينِي مِثْلَ صَلْصَلَةِ الْجَرَسِ
እዚህ ሐዲስ ላይ የተጠቀሰው ቃል "እንደ ደውል ድምፅ" የሚል ሆኖ ሳለ ሐሳውያን "ደውል" የምትለዋን ቃል ብቻ ይመዙና በመለጠቅ "ደውል የሰይጣን መዝሙር ነው፥ መላእክት ደውል ያለበት ቤት አይገቡም" ከሚሉት ዘገባዎች ጋር ሊያምታቱ ይሞክራሉ፥ “አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን የሚውለውን እንደ አንድ ነገር አርጎ መውሰድ "የማወላወል ሕፀፅ"fallacy of equivocation" ነው። "ጀረስ" جَرَسٌ እኮ እራሱ መሣሪያው ሲሆን "ሚሥለ ሶልሶለቲል ጀረሥ" مِثْلَ صَلْصَلَةِ الْجَرَس ደግሞ "እንደ ደውል ድምፅ" ማለት ነው፥ ከደውል ምሳሌ የተወሰደው ድምፁ ብቻ ሆኖ ሳለ "ደውል" በሚለው ቃል ላይ መነሻ የሆነውን "እንደ" የሚለውን መስተዋድድ ለምን መዝለል አስፈለገ? ኢማም አሥ ሡዩጢይ በዚህ መልክ እና ልክ አስቀምጠውታል፦
አል ኢትቃን ፊ ዑሉሙል ቁርኣን
"እንደ ደውል ድምፅ" የተባለው የመልአኩ ጂብሪል የክንፉ እንቅስቃሴ ድምፅ ነው"።
ተጨማሪ ናሙና ከሐዲስ ማየት ይቻላል፥ "ትርንጎ" እና "ተምር" ተክል እንጂ ሰዎች አይደሉም። ቅሉ ግን "እንደ" በሚል መስተዋድድ የተወሰነ ነገርን ለመግለጽ መጥተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 84
አቢ ሙሣ እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ቁርኣንን የሚቀራ እና የሚተገብር አማኝ "እንደ" ትርንጎ ነው፥ ሽታው መልካም እና ጣዕሙ ጣፋጭ ጥሩ ነው። ቁርኣንን የማይቀራ እና ግን የሚተገብር አማኝ ደግሞ "እንደ" ተምር ነው፥ ሽታ የሌለው እና ጣዕም ያለው ነው"።
عَنْ أَبِي مُوسَى، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " الْمُؤْمِنُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالأُتْرُجَّةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَرِيحُهَا طَيِّبٌ، وَالْمُؤْمِنُ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالتَّمْرَةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَلاَ رِيحَ لَهَا
"እንደ ትርንጎ" ማለት እና "እንደ ተምር" ማለት "ትርንጎ" እና "ተምር" ማለት ነውን? "አይ" ካላችሁ እግዲያውስ ከላይ ያለውንም ሐዲስ በዚህ ቀመር እና ስሌት ተረዱት! ሌላ ናሙና ተመልከቱ! ኢየሱስ አንበሳ ተብሏል፥ ዲያብሎስም አንበሳ ተብሏል፦
ራእይ 5፥5 እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ።
1 ጴጥሮስ 5፥8 ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ "እንደ" ሚያገሣ "አንበሳ" ይዞራልና።
ስለዚህ እንደ እናንተ ስሑት ኂስ ኢየሱስ ዲያብሎስ ነው? ቅሉ ግን "እንደ" የሚለውን መስተዋድድ መዝለል የለብንም፥ ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላል፦
መክብብ 9፥4 ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላል።
እዚህ ጋር አንበሳ የተባለው ኢየሱስ ከሆነ ከኢየሱስ ያልሞተ ውሻ ይሻላል ብለን እንሞግታችሁ? "አንበሳ" የተባለ ሁሉ ኢየሱስ ነው" ተብሎ አይደመደምም፦
2 ጢሞቴዎስ 4፥17 ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።
እዚህ አንቀጽ ላይ "አንበሳ" የተባለው አንዳንዶች "ሰይጣን ነው" ሲሉ፣ አንዳንዶች "የዱር አንበሳ ነው" ሲሉ፣ ሌሎች "ኔሮ ቄሳር ነው" ሲሉ፣ ሌሎች "ሄሉዩስ ቄሳር ነው" ሲሉ፣ ሎሎች ደግሞ "እለእክንድሮስ ነው" ይላሉ፥ አዘለም አቀፈ ኢየሱስ አንበሳ የተባለበት የዱር እንስሳት፣ ሰይጣን፣ ኔሮ፣ ሄሉዩስ፣ እለእክንድሮስ በተባሉበት ሒሣብ እንዳልሆነ ሁሉ ደውል እና እንደ የደውል ድምፅ የተባለውን አታምታቱ!
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።
✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም