ዳዊት የእሴይ ስንተኛ ልጅ ነው? 7ኛ ወይስ ስምንተኛ?

A. ሰባተኛ፦
1ኛ ዜና መዋዕል 2፥13-15 እሴይም የበኵር ልጁን ኤልያብን፥ ሁለተኛውንም አሚናዳብን፥ ሦስተኛውንም ሣማን፥ አራተኛውንም ናትናኤልን፥ አምስተኛውንም ራዳይን፥ ስድስተኛውንም አሳምን፥ ሰባተኛውንም ዳዊትን ወለደ

እዚህ ዐውደ ንባብ ላይ እሴይ ሰባት ልጆች እንዳሉት እና የመጨረሻ ሰባተኛው ዳዊት እንደሆነ ተገልጿል።

B. ስምተኛ፦
1 ሳሙኤል 16፥10-13 እሴይም ከልጆቹ ሰባቱን በሳሙኤል ፊት አሳለፋቸው። ሳሙኤልም እሴይን፦ እግዚአብሔር እነዚህን አልመረጠም፡ አለው። ሳሙኤልም እሴይን፦ የቀረ ሌላ ልጅ አለህን? አለው። እርሱም፦ ታናሹ ገና ቀርቶአል፤ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል፡ አለ። ሳሙኤልም እሴይን፦ እርሱ እስኪመጣ ድረስ አንረፍቅምና ልከህ አስመጣው፡ አለው። ልኮም አስመጣው፤ እርሱም ቀይ፥ ዓይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም፦ ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው፡ አለ። ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።

እዚህ ዐውደ ንባብ ላይ ደግሞ እሴይ ሰባት ልጆች አሳልፎ፥ ከሰባቱ ሌላ ትንሹ የመጨረሻው ዳዊት እንደሆነ ተገልጿል። ስምንተኛም እንደሆነ ቅቡል ነው።

ጥያቄአችን፦ "ዳዊት የእሴይ ስንተኛ ልጅ ነው? 7ኛ ወይስ ስምንተኛ?

✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም