በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 4፥3 ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡
مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا
"ኒካሕ" نِكَاح የሚለው ቃል “ነከሐ” نَكَحَ ማለትም “አገባ” ወይም “ተዳራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጋብቻ” ወይም “ትዳር” ማለት ነው፥ በኢሥላም ሐላል ጋብቻ በተቃራኒ ፆታ"hetero sexual" መካከል ያለ እንጂ በተመሳሳይ ፆታ"homo sexual" መካከል ያለው ጋብቻ ሐራም ነው። የሥነ-ጋብቻ ጥናት"matrimony" እንደሚያትተው የጋብቻን ሒደት በሁለት ይከፍለዋል፥ እርሱም አንድ ወንድ ለአንድ ሴት አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ጋብቻ"monogamy" እና አንድ ወንድ ለብዙ ሴት አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ጋብቻ"polygamy” ነው። ፓሎጋሚ እራሱ ለሁለት ይከፈላል፥ እርሱም አንድ ወንድ ለብዙ ሴት ጋብቻ"polyandry" እና አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ጋብቻ"polygyny” ነው። በኢሥላም አንድ ወንድ በፍትሕ እኩል ማስተዳደር ከቻለ ሁለት ወይም ሦስት አሊያም አራት ማግባት ይችላል፦
ቁርኣን 4፥3 ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ። አለማስተካከልን ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡
مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا
"ማስተካከል" ለሚለው የገባው የግስ መደብ "ተዕዲሉ" تَعُولُوا ሲሆን የስም መደቡ "ዐድል" عَدْل ነው፥ "ዐድል" عَدْل ማለት "ፍትሕ" ማለት ሲሆን አንድ ተባዕት በፍትሕ ሁለት ወይም ሦስት አሊያም አራት እንስታትን እኩል ሐቃቸውን መጠበቅ ካልቻለ ከጥብቆች ምእምናት አንዲቷን ወይም ያንን ማድረግ ዐቅም ከሌለው እጆች ንብረት ካደረጓቸው ከምእምናት ማግባት ይችላል፦
ቁርኣን 4፥25 ከእናንተም ውስጥ ጥብቆች ምእምናት የኾኑትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምእምናት ወጣቶቻችሁ ያግባ፡፡
وَمَن لَّمْ يَسْتَطِعْ مِنكُمْ طَوْلًا أَن يَنكِحَ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ فَمِن مَّا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُم مِّن فَتَيَاتِكُمُ الْمُؤْمِنَاتِ
ነቢያችን"ﷺ" ከአራት በላይ ያገቡበት ምክንያት አንደኛ እርሳቸው ያገቡት "ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ" የሚለው ከመውረዱ በፊት ነው። ሁለተኛ "ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት" የሚለው ቃል "ኢሥቲስናእ" اِسْتِثْنَاء ማለትም “ፍትቅታ”exceptional” ሆኖ የመጣ ነው፦
ቁርኣን 35፥1 ምስጋና ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ሶስት ሶስት፣ አራት አራት ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡ በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡
الْحَمْدُ لِلَّهِ فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ جَاعِلِ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا أُولِي أَجْنِحَةٍ مَّثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۚ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ሶስት ሶስት፣ አራት አራት ክንፎች ናቸው ማለት ኢሥቲስናእ ነው፥ ምክንያቱም አሏህ "በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል" ስለሚል ከአራት ክንፎች በላይ ጂብሪልን ባለ ስድስት መቶ ክንፍ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 332
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ” ጂብሪልን በተፈጥሮ ቅርፁ ባለ ስድስት መቶ ክንፍ ያለው ሆኖ አይተውታል”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ { لَقَدْ رَأَى مِنْ آيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَى} قَالَ رَأَى جِبْرِيلَ فِي صُورَتِهِ لَهُ سِتُّمِائَةِ جَنَاحٍ .
በተመሳሳይ መልኩ የነቢያችን"ﷺ" ከአራት በላይ ማግባት አሏህ ያሻው ስለሆነ ነው።
"አሏሁ አዕለም" اَللّٰهُ أَعْلَم
✍ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም