በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡4፥3

ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡
مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

"ሞኖስ" μονός ማለት "ብቻ" ማለት ሲሆን "ጋሞስ" γάμος ማለት "ጋብቻ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ሞኖ ጋሞስ" μονό γάμος ማለት "የአንድ ለአንድ ጋብቻ "Monogamy" ማለት ነው።

"ፖሎስ" πολλός ማለት "ብዙ" ማለት ሲሆን "ጋሞስ" γάμος ማለት "ጋብቻ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ፖሎ ጋሞስ" πολλό γάμος ማለት "የአንድ ለብዙ ጋብቻ "Polygamy" ማለት ነው።

የአንድ ለብዙ ጋብቻ እራሱ ለሁለት ይከፈላል፥ አንዱ "ፖሎ ጉኔ" πολλό gunḗ ሲሆን "አንድ ወንድ ብዙ ሚስት"Polygyny" ማለት ነው። በቁርኣን የተፈቀደው ፖሎ ጉኔ ነው፦

4፥3 ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡
مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

አለማስተካከልን ከተፈራ ሞኖ ጋሞስ ይበረታታል። በባብይል ፖሎ ጉኔ የተፈቀደ ነው። ይህንን መጣጥፍ ይመልከቱ፦ https://t.me/Wahidcom/2964

የአንድ ለብዙ ጋብቻ ሁለተኛው ደግሞ "ፖሎ አነር" πολλό ሲሆን "አንድ ሴት ብዙ ባል"Polyandry"ማለት ነው፥ ፖሎ አነር በቁርኣን ክልክል ሲሆን በጳውሎስ ትምህርት የተፈቀደ ነው፦

1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥12 ዲያቆናት የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ። διάκονοι ἔστωσαν μιᾶς γυναικὸς ἄνδρες,

"የአንዲት ሴት ባሎች" "Let the deacons be the husbands of one wife" የሚለው ይሰመርበት! "ባሎች" የሚለው ቃል በግሪኩም በነጠላ "አኔር" ἀνήρ ሳይሆን በብዙት ቁጥር "አንድሬስ" ἄνδρες ነው፥ "አንዲት ሴት" ብዙ ዲያቆናት ባሎች ማግባትን ጳውሎስ ስለፈቀደ በባይብል ፖሎ አነር አለ ማለት ነው። ፖሎ ጉኔን የምትቃወሙ ምን ይውጣችሁ ይሆን?

ባል እና ሚስት እያወሩ ነው...

ሚስት፦ "ፍቅሬ ሴት ከብዙ ወንዶች ጋር ስትዘወጅ ሐራም ነው፥ ወንድ ግን ከአራት ሴቶች ጋር ሲዘወጅ ሐላል ነው። ለምንድ ነው?

ባል፦ "አየሽ ፍቅሬ አንድ የቁልፍ ጋን በአራት የተለያየ ቁልፍ የሚከፈት ከሆነ ጋኑ ችግር አለበት ማለት ነው፥ አንድ ቁልፍ ግን አራት የተለያዩ ጋኖችን መክፈት ከቻለ ምርጥ ቁልፍ ነው ማለት ነው"።

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም