በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ቁርኣን 23፥100 ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ "ግርዶ" አለ፡፡
وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ
አምላካችን አሏህ ሕያው አርጎ እንደፈጠረን በሞት የሚያሞተን እርሱ ነው፥ ካሞተን በኃላ ሁላችንም ወደ እርሱ እንመለሳለን፦
ቁርኣን 22፥23 እኛም ሕያው የምናደርግ እና የምናሞት እኛው ብቻ ነን፡፡
وَإِنَّا لَنَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ
ቁርኣን 10፥56 እርሱ ሕያው ያደርጋል ያሞታልም፥ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡
هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
ቁርኣን 5፥105 የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡
إِلَى اللَّهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
"ቀብር" قَبْر የሚለው ቃል "ቀበረ" قَبَرَ ማለትም "ሸፈነ" "ደበቀ" "ሸሸገ" "ቀበረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሽፍን" "ድብቅ" "ሽሽግ" "ቀብር" ማለት ነው፥ "ቀብር" አጠቃላይ ከሞት በኃላ ከአምስቱ የስሜት ህዋሳት ባሻገር ተሸፍኖ፣ ተደብቆ፣ ተሸሽጎ፣ ተቀብሮ ያለ የአኺራህ የመጀመሪያው ደረጃ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 5
የዑስማን ነጻ ባሪያ ሃኒእ ሰምቶ እንደተረከው፦ "ዑስማን መቃብር ላይ ሲቆሙ ፂሙ በእንባ እስኪርስ ድረስ አለቀሰ፥ ለእርሱም፦ "ጀነት እና እሳት ሲዘከሩ ሳታለቅስ ለዚህ ለምን ታለቅሳለህ? ተባለ፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በእርግጥ ቀብር የአኺራህ መጀመሪያ ደረጃ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ከቀብር የዳነ ከሆነ ከዚያ በኋላ የሚመጣው ከቀብር የበለጠ ቀላል ነው፥ አንድ ሰው ከቀብር ካልዳነ ከዚያ በኋላ የሚመጣው ከቀብር የከፋ ነው።
أَنَّهُ سَمِعَ هَانِئًا، مَوْلَى عُثْمَانَ قَالَ كَانَ عُثْمَانُ إِذَا وَقَفَ عَلَى قَبْرٍ بَكَى حَتَّى يَبُلَّ لِحْيَتَهُ فَقِيلَ لَهُ تُذْكَرُ الْجَنَّةُ وَالنَّارُ فَلاَ تَبْكِي وَتَبْكِي مِنْ هَذَا فَقَالَ إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِنَّ الْقَبْرَ أَوَّلُ مَنَازِلِ الآخِرَةِ فَإِنْ نَجَا مِنْهُ فَمَا بَعْدَهُ أَيْسَرُ مِنْهُ وَإِنْ لَمْ يَنْجُ مِنْهُ فَمَا بَعْدَهُ أَشَدُّ مِنْهُ "
"አኺራህ" آخِرَة ማለት "ቀጣይ ዓለም" ማለት ሲሆን ከሞት በኃላ ያለው ዓለም ነው። አን ናዚዓት እና አን-ናሺጧት በተባሉ የሞት መላእክት ስንወሰድ በቀብር "አል ሙንከር" الْمُنْكَر እና "አን ነኪር" الْنَّكِير የተባሉ መላእክት ለሰው፦ "ጌታህ ማን ነው? ዲንህ ምንድን ነው? ነቢይህ ማን ነው?” ብለው ይጠይቃሉ። አማኝም ከሆነ፦ "ጌታዬ አሏህ ነው፣ ዲኔ ኢሥላም ነው፣ ነቢዬም የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ነው" ብሎ ሲመልስ ለእርሱ ጀነት እዲገባ ይከፈትለታል፥ ከሓዲ ከሆነ፦ "ዐላውቅም፣ ዐላውቅም፣ ዐላውቅም" ብሎ ሲመልስ ለእርሱ እሳት እዲገባ ይከፈትለታል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 158
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 107
"በርዘኽ" بَرْزَخ ማለት ሁለት ነገርን እንዳይገናኝ በመካከላቸው ያለ "ጋራጅ"partition" ነው፥ ለምሳሌ፦ ጥቁር ባሕር፣ ባልቲክ ባሕር፣ ቀይ ባሕር፣ ሜድትራኒያን ባሕር፣ ፓስፊክ ውቂያኖስ፣ አትላንቲክ ውቂያኖስ እና የሕንድ ውቂያኖስ በውስጣቸው መራራ ውኃ እና ጣፋጭ ውኃ ይዘዋል። እነዚህ ሁለቱ ባሕሮች እንዳይገናኙ በመካከላቸው በርዘኽ አለ፦
ቁርኣን 55፥19 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡ مَرَجَ الْبَحْرَيْنِ يَلْتَقِيَانِ
ቁርኣን 55፥20 እንዳይገናኙ በመካከላቸው "ጋራጅ" አለ፡፡ አንዱ ባንዱ ላይ ወሰን አያልፉም፡፡ بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌ لَّا يَبْغِيَانِ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ጋራጅ" ለሚለው የገባው ቃል "በርዘኽ" بَرْزَخ ሲሆን "ግርዶ" "መለያ" "ክልል" ማለት ነው። በተመሳሳይም ሁሉም ሰው ወደ አሏህ ከተመለሰ በኃላ አማንያን ያሉበት ጀናህ እና ከሓዲያን ያሉበት እሳት በመካከላቸው እንዳይገናኙ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በርዘኽ አለ፦
ቁርኣን 23፥100 ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ "ግርዶ" አለ፡፡ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ግርዶ" ለሚለው የገባው ቃል "በርዘኽ" بَرْزَخ ሲሆን ልክ የእናት ማኅፀን ከፅንስ እስከ ልደት ጊዜአዊ መቆያ እንደሆነ ሁሉ በርዘኽም ከሞት እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ያለ መካከለኛ ቀጠና"intermediate zone" ነው። በጊዜአዊ መቆያ የገነት ሰዎች እና የእሳት ሰዎች የንግግር ልውውጥ ያረጋሉ፦
ቁርኣን 7፥44 የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎች፦ «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፡፡ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ ይጣራሉ፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ
ቁርኣን 7፥50 የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎች፦ «በእኛ ላይ ከውኃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ጣሉልን» ብለው ጠሩዋቸዋል፡፡ እነርሱም «አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም አድርጓቸዋል» ይሏቸዋል፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ النَّارِ أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَنْ أَفِيضُوا عَلَيْنَا مِنَ الْمَاءِ أَوْ مِمَّا رَزَقَكُمُ اللَّهُ ۚ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ حَرَّمَهُمَا عَلَى الْكَافِرِينَ
የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎችን የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎችን ቢያነጋግሩም በመካከላቸውም እንዳይገናኙ "ግርዶሽ" አለ፦
ቁርኣን 7፥46 በመካከላቸውም "ግርዶሽ" አለ። وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ
አምላካችን አሏህ ከእሳት ቅጣት ይጠብቀን! የጀነት ያድርገን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም