በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
ቁርኣን 60፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼን እና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርገችሁ አትያዙ፡፡
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمْ أَوْلِيَاءَ
የተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ተከታዮች በኢብራሂም እና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት ምእምናን መልካም መከተል አለን፦
ቁርኣን 60፥4 በኢብራሂም እና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት ምእምናን መልካም መከተል አለቻችሁ፡፡
قَدْ كَانَتْ لَكُمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ فِي إِبْرَاهِيمَ وَالَّذِينَ مَعَهُ
ኢብራሂም እና ተከታዮቹ ለሕዝቦቻቸው ያስተላለፉት መልእክት አላህ አንድ ብቻ የሚለውን የተውሒድ እሳቤ እስኪያምኑ ድረስ በእነርሱ እና በሕዝቦቻቸው መካከል በራእ ማድረግን ነው፦
ቁርኣን 60፥4 ለሕዝቦቻቸው «እኛ ከእናንተ እና ከአላህ ሌላ ከምታመልኩት ንጹሓን ነን፡፡ በእናንተ ካድን፡፡ በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛ እና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፡፡» ባሉ ጊዜ መልካም መከተል አለቻችሁ፡፡
إِذْ قَالُوا لِقَوْمِهِمْ إِنَّا بُرَآءُ مِنكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةُ وَالْبَغْضَاءُ أَبَدًا حَتَّىٰ تُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَحْدَهُ
"ንጹሓን" ለሚለው የገባው ቃል "ቡራእ" بُرَآء ሲሆን "በሪእ" بَرِيء ማለትም "ንጹሕ" ለሚለው ብዜት ነው፥ "በራእ" بَرَاء የሚለው ቃል እራሱ "በሪአ" بَرِئَ ማለትም "ጠላ" "ራቀ" "ተወ" "ነጻ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መጥላት" "መራቅ" "መተው" "ንጹሕ" ማለት ነው፦
ቁርኣን 43፥26 ኢብራሂምም ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ፦ «እኔ ከምታመልኩት ሁሉ ንጹሕ ነኝ፡» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡
وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ إِنَّنِي بَرَاءٌ مِّمَّا تَعْبُدُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ንጹሕ" ለሚለው የገባው ቃል "በራእ" بَرَاء ሲሆን የአሏህን ጠላቶችን በዲን ነጥብ እና ጉዳይ ላይ በራእ አለማድረግ በአሏህ ላይ ማመጽ ነው፥ ከኢሥላም ውጪ ያሉት አላህ አንድ ብቻ የሚለውን የተውሒድ እሳቤ እስኪያምኑ ድረስ በእኛ እና በእነርሱ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር አለ። ቤተሰቦቻችንን ከአሏህ ቅጣት ምንም የማናስመልጥ ስንሆን ለእነርሱ በእርግጥ ምሕረትን እንለምናለን፦
ቁርኣን 60፥4 ኢብራሂም ለአባቱ «እኔ ለአንተ ከአላህ ቅጣት ምንም የማልጠቅም ስኾን ለአንተ በእርግጥ ምሕረትን እለምንልኻለሁ» ማለቱ ብቻ ሲቀር፡፡ «ጌታችን ሆይ! በአንተ ላይ ተመካን፡፡ ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው፤» ባለው ተከተሉት፡፡
إِلَّا قَوْلَ إِبْرَاهِيمَ لِأَبِيهِ لَأَسْتَغْفِرَنَّ لَكَ وَمَا أَمْلِكُ لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن شَيْءٍ ۖ رَّبَّنَا عَلَيْكَ تَوَكَّلْنَا وَإِلَيْكَ أَنَبْنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ
የአሏህ ብቻ ሐቅ እና ገንዘብ የሆነው አምልኮ ለሌላ ምንነት እና ማንነት የሚያጋሩ ሰዎች የአሏህ ጠላቶች ናቸው፥ በዚህ ወንጀል የተዘፈቁ እስከ ዝንተ ዓለም ለእሳት ይዳረጋሉ። ከሓዲያን የአሏህ ጠላቶች ስለሆኑ ለአማንያንም በእርግጥ ግልጽ ጠላቶች ናቸው፦
ቁርኣን 41፥19 የአላህ ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን አስታውስ፡፡
وَيَوْمَ يُحْشَرُ أَعْدَاءُ اللَّهِ إِلَى النَّارِ
ቁርኣን 4፥101 ከሓዲዎች ለእናንተ በእርግጥ ግልጽ ጠላቶች ናቸውና፡፡
إِنَّ الْكَافِرِينَ كَانُوا لَكُمْ عَدُوًّا مُّبِينًا
ቁርኣን 60፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼን እና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርገችሁ አትያዙ፡፡
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمْ أَوْلِيَاءَ
"ወሊይ" وَلِىّ ማለት "ወዳጅ" "ረዳት" "ጓደኛ" ማለት ሲሆን "አውሊያእ" أَوْلِيَاء ደግሞ "ወዳጆች" "ረዳቶች" "ጓደኞች" ማለት ነው፥ "ወላእ" وَلَاء የሚለው ቃል እራሱ "ወሊየ" وَلِيَ ማለትም "ረዳ" "ወደደ" "ቀረበ" "ተጎዳኘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መርዳት" "መውደድ" "መቅረብ" "መጎዳኘት" ማለት ነው፦
ቁርኣን 9፥71 ምእመናን እና ምእመናት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ "ረዳቶች" ናቸው፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ረዳቶች" ለሚለው የገባው ቃል "አውሊያእ" أَوْلِيَاء እንደሆነ ልብ አድርግ! ለአማኝ ወንድሞች እና ለአማኝ እኅቶች "ወዳጆች" "ረዳቶች" "ጓደኞች" ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ነው። በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ አማንያን አሏህን እና መልእክተኛው የሚዘልፉ ከቤተሰባቸው ቢሆኑ እንኳን አይወዳጁም፦
ቁርኣን 58፥22 በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህን እና መልእክተኛው የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡
لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ
እንግዲህ "አል ወላእ ወል በራእ" الْوَلَاء وَالْبَرَاء የሚለው የተውሒድ መርሕ "ለአሏህ ብሎ መወደድ እና መጥላት" ማለት ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42 ሐዲስ 86
አቢ ኡማማህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ለአሏህ ብሎ የወደደ እና የጠላ እንዲሁ ለአሏህ ብሎ የሰጠ እና የነፈገ የተሟላ ኢማን ይኖረዋል"።
عَنْ أَبِي أُمَامَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ “ مَنْ أَحَبَّ لِلَّهِ وَأَبْغَضَ لِلَّهِ وَأَعْطَى لِلَّهِ وَمَنَعَ لِلَّهِ فَقَدِ اسْتَكْمَلَ الإِيمَان
ለአሏህ ብሎ መስጠት ከእዩልኝ እና ከስሙልኝ ነጻ የሆነ ልግስና ሲሆን ለአሏህ ብሎ ለአልባሌ ነገር ከመስጠት የነፈገ ከጥፋት መታደግ ነው፥ በተመሳሳይ ለዘሩ፣ ለብሔሩ፣ ለዘውጉ እና ለነፍሥያው ብሎ ሳይሆን ለአሏህ ብሎ አሏህ የሚጠላውን ነገር የሚጠላ እና አሏህ የሚወደውን የሚወድ የተሟላ ኢማን አለው።
አምላካችን አሏህ ሐቅን በማንገስ ባጢልን በማርከስ ወላእ እና በራእ የምናደርግ ያድርገን! ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ የሆነ ኢኽላሱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም